በስመአብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ዘጸ. 15-፡-27
ቃሉን የተናገረው አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት በግልጽ ማስረዳት ነው፡፡ ትእዛዙን ብታደምጥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ በግብፃዊያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ፈውስ የሚለው ቃል ከበሽታ መዳን ጤናን ማግኘት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህዝብ ካለ በበሽታ ሊቀጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‹‹ባትሰሙኝ ትእዛዜን ሁሉ ባታደርጉ ሥርዓቴንም ብትንቁ፣ ፍርሐትን፣ ክሳትንም፣ ዓይናችሁንም የሚያፈዝ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ይላል›› ዘሌዋ. 26፡14-፡-16
ትእዛዙን የሚጠብቅ ካለግን… ህማም ሁሉ ካንተ ይርቃል የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ ባንተ ላይ አይደርስብህም ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ዘዳ. 7-፡-15
በሽታ በተለያየ መንገድ ሊከሰት ይችላል፡፡ ንፅህናን ባለመጠበቅ ሊመጣ ይችላል፡፡ እራስን ለእግዚአብሔር ባለማስገዛትም ሊመጣ ይችላል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በበሽታ ከተቀጡ መካከል ስንመለከት፤-
1.እህተ ሙሴ ማርያም እግዚአብሔር ባከበረው በነብዩ ሙሴ ላይ የማይገባትን በመናገሯ እግዚአብሔርንም ባለመፍራቷ በለምጽ ተመትታለች፡፡ ዘኁል. 12፡-10
2.ነብየ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ ኤልሳ እየዋሸ የማይገባውን ንብረት በመውሰዱ የንዕማንን ለምፅ በዘሩ ላይ ተጣብቆበት የኖረ እንደበረዶም ለምጻም የሆነ ጊያዝን እንመልከት፡፡ 2ኛነገ. 5-፡-25-27
3.የቤተመቅደሱ አገልጋይ ካህኑ ዘካርያስ የእግዚአብሔርን መልክተኛ ባለመታዘዙ ከ275 ቀናት በላይ ድዳ ሆኖ ተቀጥቷል፡፡ ሉቃ. 1-፡-20
4.ሰርግዮስ የተባለ አገረ ገዥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በፈለገ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይ አገረ ገዥውን እንዳያምን የእግዚአብሔርንም ቃል እንዳይሰማ ጳውሎስንና በርባናስን ተቃወማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳውል የተባለ ጳውሎስ ተንኮል፣ ክፋት የሞላብህ የጽድቅም ጠላት ስለሆንክ ዓይንህ አይይ አለው፡፡ ዓይኑም ታወረ ጽድቅን በመቃወሙ ታመመ፡፡ ሐዋ. 13-፡- 11
የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች በተለያየ ምክንያት በሽታ በተለያዩ ሰዎች ቢከሰትም ፈዋሹ እግዚአብሔር መሆኑ ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን ድረስ በስፋት ጽፈውልናል፡፡ በዘመነ ሥጋዌም ኢየሱስ ክርስቶስ ከታመሙት እና በደዌ ከተያዙት አልፎ የሞቱትንም ጭምር ከሙታን መካከል እንዳስነሳቸው የአምላካችን አዳኝነቱም ቅዱስ መፅሐፍ በስፋት ይገልጥልናል፡፡

- ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ ፈውሷል ማቴ. 8-፡-16፣ ዮሐ. 4-፡-50
- ኢየሱስ ክርስቶስ በመዳሰስ ፈውሷል፡፡ ሉቃ. 5-፡-13
- ኢየሱስ ክርስቶስ እጁን በመጫን ፈውሷል፡፡ ማር. 6-፡-5
- ኢየሱስ ክርስቶስ ጭቃን በመቀባት ፈውሷል፡፡ ዮሐ. 9-፡-6-7
- ኢየሱስ ክርስቶስ በምራቁ ፈውሷል፡፡ ማር. 8-፡-23
ፈውስ ለማን ተሰጥቷል?
እግዚአብሔር
አምላካችን ከክፉ በሽታ፣ ደዌያት እኩያን አጋንንት ነፃ እንድንወጣ አስቀድሞ ነቢያትን በመላክ በኋላም ሐዋርያትን በመተካት እንድንፈወስ አድርጎናል፡፡ የፈውስ ስጦታ ለቤተክርስቲያን ተሰጥቷል፡፡ 1ኛ ቆሮ. 12-፡-9፣ 12-፡-27-30
ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ድውያንን እንዲፈውሱ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡ በእርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ስልጣን ሰጣቸው እንዲል ማቴ. 10-፡-1 ሐዋርያትም ወንጌል እያስተማሩ በሽተኞችን፣ ድውያንን እየፈወሱ ሙታንንም ሳይቀር አስነስተዋል፡፡ ከተፈወሱት መካከል፡-
1ኛ. ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ ለፀሎት ወደ ቤተመቅደስ በወጡበት ሰዓት በቤተመቀደሱ አጠገብ ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ ሰው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስ እልሀለሁ በማለት ቀኝ እጁን ይዞ እንዳስነሳው ይነግረናል፡፡ ሐዋ. 3-፡-1-8
2ኛ. ቅዱስ ጳውሎስ ልስጥራን በተባለ ቦታ ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ አንካሳ የነበረ ሂዶ የማያውቅ ሰው ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም አለውና ብድግ ብሎ መመላለስ ጀመረ ይላል፡፡ ሐዋ. 14-፡-8-10
3ኛ. ቅዱስ ጴጥሮስ ኤንያ የተባለ 8 ዓመት ሙሉ አልጋ ላይ ተኝቶ የነበረ ሽባ ኤንያ ሆይ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል ተነሳ አለው ወዲያውኑም ተነሳ፡፡ ሐዋ. 9-፡-32-34
4ኛ. በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል ደግ ሴት በምፅዋቷ የታወቀች ታማ ሞተች ቅዱስ ጴጥሮስም ተንበርክኮ ፀለየ ወደ ሬሳውም ዞር ብሎ ጣቢታ ሆይ ተነሽ አላት ወዲያውም ተነሳች፡፡ ሐዋ. 9-፡-36-41
5ኛ. ሳይታመም በድንገተኛ በእንቅልፍ ምክንያት አንቀላፍቶ ወድቆ የሞተው አውጤክስ የተባለ ጎበዝ ነበር ቅዱስ ጳውሎስም መሞቱን ሰምቶ ከደርብ ወርዶ ነፍሱ አለችበት አትዘኑ ብሎ በማፅናናት ከሞት አስነሳው፡፡ ሐዋ. 20-፡- 9-11
ፈውስ ለሐዋርያት ለ70 አርድዕት የተሰጠ ሲሆን የሐዋርያትም ሆነ የሰባ አርድዕት የመፈወስ (የማዳን) መንገዱ ፀሎት ከማድረግና የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከመጥራት ሌላ መንገድ እንዳልተከተሉ ልብ ይሏል፡፡ ሌላው ዛሬም ድረስ ቤተክርስቲያናችን የምትጠቀመው መፅሐፈ ቀንዲልን በዘይት (ቅብዕ) እየደገሙ ድውያንን ይፈውሱ ነበር፡፡ ማር. 6-፡-13
የታመመ ማንም ቢኖር የቤተክርስቲያንን ቀሳውስትን ወደእርሱ ይጥራ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይፀልዩለት እንዲል፡፡ ያዕ. 5-፡-14 የፈውስ አገልግሎት ስመ እግዚአብሔርን በመጥራት በተዘጋጀ ውኃ ቅዱስ ቅባት ጨምሮ ለታመመ እንዲሁም በኃጢአት ልጅነቱን ያስወሰደ ሰው ካለ እነዚህን አንድ ላይ አድርጎ የቀንዲልና የቄደርን ስርዓት እንዲፈፀምለት ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም በፈለቀው ጠበል በመጠመቅ ሰው ከተለያየ በሽታ ይፈወሳል፡፡ ከዚህ ውጭ በቅጠል፣ በስራስር፣ በሸኮና፣ በአጥንት፣ በደሮ፣ በበግ ብሎ ፈውስ የለም፡፡

ለመፈወስ ወይም ለመዳን ምን ያስፈልጋል?
1.እምነት
ያለእምነት
የሚደረግ ነገር አይኖርም፡፡ እምነት መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ አሚንሰ መሰረት ይእቲ (እምነት መሠረት ናት) እንዲል እንዲሁም ወዘእንበለ ተአምኖሰ ኢይትከሃል ያስምርዎ ለእግዚአብሔር (ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይቻልም፡፡ ዕብ. 11-፡-6 በማመናቸው ምክንያት የተፈወሱትን ስንመለከት፡-
ለ12 ዓመት በደም መፍሰስ በሽታ ስትሰቃይ የነበረችው ሴት የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች በልቧም ልብሱን ብቻ የዳሰስኩ እንደሆነ እድናለሁ ትል ነበር፡፡ ኢየሱስም አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል አላት፡፡ ወዲያውኑ ዳነች ደሙም ቆመላት፡፡ ማቴ. 9-፡-20-23
የመቶ አለቃው ልጅ ታሞ ሽባ ሆኖ ይሰቃይ ነበር፡፡ አባቱም ልጄን አድንልኝ ብሎ ለመነ፡፡ ኢየሱስም መጥቼ እፈውሰዋለሁ ባለው ጊዜ ቃል ብቻ ተናገር ብላቴናዬ ይፈወሳል ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን ፍፁም አዳኝ መሆኑን በማመን ለመነ፡፡ ጌታም ትልቅ እምነት አለህ እንዳመንክ ይሁንልህ አለው፡፡ ብላቴናውም ተፈወሰ፡፡ ማቴ. 8-፡-5-13
vበመንገድ ዳር ላይ ተቀምጦ ይጮህ የነበረው ዓይነ ስውር ወደ ኢየሱስ መጣ ኢየሱስ እንደሚያድን ተረድቶ መምህር ሆይ አይዘንድ እርዳኝ ብሎ ለምኖታል፡፡ ኢየሱስም እምነትህ አድኖሃል አለው ወዲያውኑም አየ፡፡ ማር. 10-፡-47-52

2.ንስሐ
የኃጢአት ስርየት
ማግኘት ማለት ነው በስህተትም ሆነ በድፍረት የተደረገውን ኃጢአት አምኖ መፀፀት እራስን ለካህን ማሳየት መንፈሳዊ ስራ ነው፡፡ በኃጢአት ከወደቁ በኋላ ያለንስሐ ዳግም ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት አይቻልም፡፡ ንስሐ አንዱ የመዳን መንገድ ነው፡፡ ሰዎች ተሸክመው ወደጌታ የመጣውን ሽባ ስንመለከት ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ብሎ ፈውሶታል፡፡ ማር. 2-፡-1-12 ቅዱስ ያዕቆብም እርስ በእርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ ይላል፡፡ ያዕ. 5-፡-16
3.ለመዳን ፈቃደኛ መሆን እና መለመን
እግዚአብሔር
በጎ ፈቃዱን መልሶብን አያውቅም፡፡ አዳኝነቱን ተረድተን መለመን ግን የሰዎች ድርሻ ይሆናል፡፡ ለ38 ዓመት ታሞ የነበረው በሽተኛ ልትድን ትወዳለህን? ባለው ጊዜ ድውዩም ጌታ ሆይ ወደውኃው የሚወስደኝ ሰው የለም እንጂ አዎ ብሎ ነበር የመለሰለት፡፡ ፈቃደኛ መሆኑን አውቆ ፈውሶታል የተሸከመችህ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ብሎታል፡፡ ዮሐ. 5-፡-5-9
vበቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ንጉስ ስለልጁም መፈወስ (መዳን) ኢየሱስ ክርስቶስን ለምኗል፡፡ ስለልጁ መዳን የጌታችን አዳኝነት እና ፈዋሽነትን በፍፁም ልቡ አምኖ ለምኗል ልጁም ተፈውሶለታል፡፡ ዮሐ. 4-፡-46-50

ማጠቃለያ
የሃይማኖት
ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር ሰዎች ሁሉ እውነተኛውን እውቀት እንዲያገኙ መጣር ስለሆነ ይህ አጫጭር የእውቀት ምንጭ ወይም በራሪ ወረቀት በእጅዎ ደርሶ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ እንዲያውቁ እና በዚህ አድራሻ እንዲጠቀሙ አዘጋጅተን ያቀረብን ሲሆን ተከታታይ ትምህርት ሰጪ በራሪ ወረቀቶችን ለማቅረብ እንሞክራለን ከጎናችን ይሁኑ!!!
በም.ቅ.ሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተጸሎት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ውስጥ ወር በገባ ከ1-3 በምህላ ፀሎት በስብከት በ5፣ በ7፣ በ12፣ በ16፣ በ21፣ በ23፣ በ28 እና በ29 ጥያቄና መልስ፣ ምስክርነት፣ ዝማሬና ስብከት እንዲሁም በእነዚህ ቀናት ጧፍ በማብራት በልዩ ጉባኤ የቅዱሳንን ዝክር በመዘከር ዕለቱን እናክብራለን፡፡ እንዲሁም ቀንዲልና ቄደር ጥምቀትን በመጠመቅ ለነፍስዎ ዋጋ ያግኙ፡፡ ይምጡና ይጠቀሙበት፡፡ /ማቴ. 51-፡-12/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

አድራሻ፡-
ከቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተ/ክርስቲያን ዝቅ ብሎ ያገኙናል
በም.ቅዱ. የሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተጸሎት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ፡-/
0911-877059/ 011-157-2581/ 0920-744622
ጉለሌ ክ/ከተማ/አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
E-mail:-Yemm2000@gmail.com
Website:- www.eotcyemm.org
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000142482618

No comments:
Post a Comment