Saturday, October 09, 2021


 

ይህን መልዕክት ያንብቡ

 ሃይማኖታችሁን ለምትወዱ ሁሉ ይህ የጽድቅ ፍሬ ጥሪ ይድረሳችሁ አንብቡት፠ጥሪዬ ደስ ላላችሁ እንግዲህ ምን እናድርግ? ሉቃ ም3ቁ10 የእኛ ድካም ምን እንደሆን ቅዱስ ጰውሎስ  በ2ኛ ቆሮ ም6ቁ8 ላይ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ እራሳችንን እናናውጣለን በሃይማኖታችሁ ቁሙ እኛ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን  ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን የምንሞት ስንመስል እንሆ ሕያዋን ነን የተቀጣን ስንመስል ግን አይደለንም ሐዘነተኞች ስንመስል ዘወትር ደስተኞች ነን ድሆች ስንባል ብዙዎችን  ባለጠጎች እናደርጋለን አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው በማለት ያስተምረናል ይህ ምስጢር ከገባችሁ እኛ የምንለምናችሁ የጽድቅን ሥራ በእውነት ሰርተን እንዳን ነው ቸሩ አምላካችን ፈጣርያችን የድንግል ማርያም ልጅ ልጆቹ ያድርገን አሜን፠፠፠እግዲህ ምን እናድርግ እግዚአብሔርን ደስ የሚአሰኙ አምስት መልካም ሥራዎች አሉ፠ 1ኛወንጌሉ ይሰበክ     በማቴ ም24ቁ14 ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካልና እልካችኁለሁ አለ በማቴ ም11ቁ6 ለድሆች ወንጌል ይሰበካል በእኔ የማይስናከል ብፁዕ ነው ይላል ይህንን ቃል መሠረት በማድግ ሰዎች መሬታቸውን ቤታቸውን እየሸጡ በሐዋርያት እግር ሥር ያደርጉ ስለነበር የወንጌል ስብከት ኦንዲስፋፋ አስተዋጾ አድርገዋል ምንያቱም አንዳንዶችን ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ ይላልየይሁዳ ም1ቁ22  እነግዲህ ለወንጌል አገልግሎት ምንአድርገዋል  2ኛስለ ቤተ ክርስቲያን ሥራ፠  ቤተ ክ ማለት የክርስቲያኖች ቤት የእግዚአብሔር ማደርያ ማለት ነው እንዲህ አለ ወደተራራ ውጡ እንጨትንም አምጡ ቤቱንም ሥሩ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል እኔም እመሰገንበታለሁ በማለት ደስ የሚአሰኜውን ሥራ ተናግሮአል ት ሐጌ ም1ቁ8 ቅዱስ ጳውሎስም የቀረውን ነገር ሳልቆጥር እለት እለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሀሳብ ነው ይላል 2ኛ ቆሮ ም11ቁ28  ለዚህ አገልግልት ዋጋ የሚከፍሉ ሁሉ ያተርፋሉ ሉቃ ም6ቁ38 በተትረፈረፈው መስፈርያ ትታቀፋላችሁ ይላልና ይህን እንሥራ  3ኛየአብነት ትምህርት አገልግሎት፠   ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር መከሩ ብዙነው ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው  ሉቃ ም10ቁ2 እነዚህ እንዲበዙ ካላስተማርን ቤተ ክርስቲያን ትዘጋለች ምክንያቱም በምድር የማሰር በሰማይ የመፍታት ሥልጣን ተስጥቶአቸዋል ማቴ ም18ቁ18 አገልጋይ እናፍራ ለዚህም ዋጋ ይክፈሉ 4ኛሁል ጊዜ ድሆችን ስለመርዳት   እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ድሆች ከምድሪቱ አያልቁምና ለተቸገረው ሁሉ እጅህን እንድትፈታ አዝዝሃለሁ ይላል ኦ ዘዳ ም15ቁ11 የእርሱን ትእዛዝ በመጠበቅ መዳን እንደምንችል ብራብ አበላችሁኝ ብጠማ አጠጣችሁኝ ብታረዝ አለበሳችሁኝ ጌታ በድሀ ተመስሎ ይነግረናል ማቴ ም25ቁ34 የሃይማኖት መገለጫው ሥራ ነው ያዕቆ ም2ቁ14 5ኛ አስራት በኩራት ስለ መክፈል    እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም እናንተ ግን ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኁል ሥርዓቴንም አልጠበቃችሁም ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደእናንተ እለሳለሁ እነርሱም በምንድነው የምንመለሰው አሉ በአስራትናበኩራት ነው ሰው እግዚብሔርን ይሰርቃልን እናንተ ግን እኔን አሥራት ኩራቱን ሰረቃችሁኝ ስለዚህም በእርግማን እርጉሞች ትሆናላችሁ ይላል ት ሚልክያስ ም3ቁ7 ቅዱስ ጳውሎስ ታላቁ አባታችን አብርሃም አሥራት በኩራቱን አወጣ ተባረከም ይላል ዕብ ም7ቁ6 ይህ ሙሉ ጤና አግኝተን ለምንሠራ ሁሉ የግዴታ ትዕዛዝ ነው ሕይወትም ነው ኦ ዘፍ ም28ቁ20 ያዕቆብ ተሳለ እግዚአብሔር ፈጸመለት ይላል ውድ በሃይማኖትለምትኖሩ ወገኖች ከዚህ በላይ የዘረዘርኩአቸው አምስት አርዕስቶች የግዚአብሔር የሚወዳቸው በጎ ሥራዎች ናቸው እስቲ እግዚአብሔርን የምቶዱ ሁሉ በማርያም ለብዙ ሰው ሸር ሸር ሸር አድርጉትና ሰው ሁሉ ሰምቶ ይጸደቅ ሰይጣን ይቃጠል ውድ ወገኖቼ ቅዱስ ሲኖዶስ በፈቀደልንና ጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈልን ደብዳቤ መሠረት ለዚሁ መልካም ሥራ አራት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ከፍተናል ንግድ ባንክ 1000425516969 አቢሲኒያ ባንክ 73744075 አዋሽ ባንክ 01320550399800 ወጋገን ባንክ 0898056730301 Y E M M ወይም የ እ ማ ማ  ብላችሁ መላክ ትችላላችሁ ስልክ0925892589 0920744622 0911147521 በዚህ ስልክ ገቢያደረጋችሁበት ደረሰኝ በቴሌግራም ላኩ የሃይማኖት እውቀት ለሁሉም ዘኦርቶዶክስ የሚለውን ሚዲያ ተከታሉ በየሳምንቱ ረቡዕ ማታ በኦ ተ ቤ ቴሌብዥን ከምሽቱ 2ሰአት እስከ3 ሰአት ተከታተሉ ስለ ትብብራችሁ ከልብ አመሠግናለሁ ከእርሶጋር አብረን እንሰራለን የምትሉኝ ሁሉ በኮሜት ድጋፋችሁን ግለጹልኝ የማኅበሩ የዕድሜ ልክ አባል ለመሆን በእመቤታችን ዕድሜ 64 000 የክብር አባል ለመሆን በየወሩ 120 በክርስቶስ ቤተሰቦች ልክ ቁዋሚ አባል በየወሩ 21ብር በእማማ ድንግል ማርያም ስም የሚከፈለው በባንክ ነው ሕጋዊ ደረሰኝ ይሰጣል አብረን እንስራ።ሊቀ ትጉ     መ ር ገ /መስቀል ኃ /መስቀል Memehir Gmeskel የማኅበሩ በሥራችና የበላይ ኃላፊ፠

Memehir Gmeskel Media

Tuesday, March 10, 2020

ምኩራብ


የዓብይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት
  •   ምኩራብ ማለት የአይሁድ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት እንዲሁም ታላቅ አዳራሽ ማለት ሲሆን ለአምልኮና ለትህምህርት መማሪያ ይገለገሉበት ነበር፡፡ ምኩራብ በአለቆች ይመራ ነበር፡፡ (ማር 5÷22፣ ዮሐ 3÷14-15,18÷8) በእየሳምንቱ ሕዝቡ ሁሉ በምኩራብ ይሰበሰቡ ነበር (ሉቃስ 4÷16፣ የሐ.ሥ 15÷21) ወንዶችና ሴቶች ለእየብቻቸው ይፀልዩና ይቆሙ እንዲሁም ይቀመጡ ነበር፡፡
  • ታዲያ ይህ ሳምንት ለምን ምኩራብ ተባለ? ሲባል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምዋለ ስብከቱ ለማስተማር ወደ ምኩራብ ገብቶ ነበርና ለዚያ መታሰቢያ እንዲሆን ምኩራብ ተብሏል (ማቴ 4÷23፣ ማር 1÷21፣ ሉቃ 4÷15)

ቅድስት


የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ሣምንት ቅድስት ይባላል፡፡

  • ቅድስት ማለት የተቀደሰች፣ የተባረከች፣ ንጽሕት፣ ልዩ የተመሰገነች ማለት ነው፡፡
  • ቅድስት የተባለበት ምክንያት ‹‹ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ (ኢዩ 1÷14) ብሎ በነቢዩ በኢዩኤል አድሮ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾማት ጾም ስለሆነች ቅድስት ትባላለች፡፡
  • እንዲሁም የዲያብሎስን ፈተና ድል ለመንሳት በቅድስት ከተማ በኢየሩሳሌም በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ጫፍ የቆመባት ዕለት ሰው ጾምን ጾሞ እንደፈጣሪው ፈተናን ድል ነስቶ ቅድስናንና ክብርን ያገኛል፡፡ ለምን ብየ ቅድስቴን ጾምኳት እንዲሉ መጾም ቅድስናን ለማግኘት ነውና፡፡