
1ኛ. የአብያተክርስቲያናትና የገዳማት ድጋፍ
በሀገረ
ስብከት፣ በወረዳ፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጽፈው ለጽ/ቤታችን ጥያቄ ለአቀረቡ ሁሉ በየተራቸው ለማስተናገድ ሞክረናል፡፡
በዚህም መሠረት በ2009 ዓ.ም በ23 /ሃያ ሶስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ167 /አንድ መቶ ስልሳ ሰባት/ የገጠር አብያተክርስቲያናትና
ገዳማት በ2010 ዓ.ም በ16 /አስራ ስድስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ102 /ለአንድ መቶ ሁለት/ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና
ገዳማት 5,000,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር) በህጋዊ ደረሰኝ እንዲረዱ አድርገናል፡፡
2ኛ. በንዋየ ቅድሳት የተረዱ
ለ10,098
/ለአስር ሺህ ዘጠና ስምንት/ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በጧፍ፣ በእጣን፣ በሻማ፣ በዘቢብ፣፣ በአልባሳት፣ በመጎናጸፊያ፣ በጃንጥላ
ወዘተ ለመርዳት የወጣው በገንዘብ ሲተመን ብር 216,027.00 (ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሃያ ሰባት ብር) እንዲረዱ አድርገናል፡፡
3ኛ. ለአብነት መምህራን የድጎማ ደመወዝ
ለ12
/አስራ ሁለት/ የአብነት መምህራን በአሉበት ቁጭ ብለው እንዲያስተምሩ ለማድረግ 26,000.00 (ሃያ ስድስት ሺህ) ብር ከፍለናል፡፡
4ኛ. መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሚማሩ መምህራን
ለ40
/አርባ/ መምህራን ወርሃዊ ክፍያ 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር) የተከፈለ ሲሆን ለ3 ዓመት ተምረው ይመረቃሉ፡፡