Thursday, August 30, 2018

የሥራ ክንውን መረጃ

   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር መስራችና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ትጉ. መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል አስተባባሪነትና መሪነት ሰጪዎችንና ተቀባዮችን በማገናኘት በገንዘብና በማቴሪያል ለገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት እንዲሁም ለችግረኛ ወገኖች የተሰጠው ድጋፍ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል የ2009 እና የ2010 ዓ.ም የሥራ ክንውን ሪፖርት በአጭሩ እናቀርባለን፡፡


1ኛ. የአብያተክርስቲያናትና የገዳማት ድጋፍ

በሀገረ ስብከት፣ በወረዳ፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጽፈው ለጽ/ቤታችን ጥያቄ ለአቀረቡ ሁሉ በየተራቸው ለማስተናገድ ሞክረናል፡፡ በዚህም መሠረት በ2009 ዓ.ም በ23 /ሃያ ሶስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ167 /አንድ መቶ ስልሳ ሰባት/ የገጠር አብያተክርስቲያናትና ገዳማት በ2010 ዓ.ም በ16 /አስራ ስድስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ102 /ለአንድ መቶ ሁለት/ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት 5,000,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር) በህጋዊ ደረሰኝ እንዲረዱ አድርገናል፡፡ 



2ኛ. በንዋየ ቅድሳት የተረዱ

ለ10,098 /ለአስር ሺህ ዘጠና ስምንት/ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በጧፍ፣ በእጣን፣ በሻማ፣ በዘቢብ፣፣ በአልባሳት፣ በመጎናጸፊያ፣ በጃንጥላ ወዘተ ለመርዳት የወጣው በገንዘብ ሲተመን ብር 216,027.00 (ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሃያ ሰባት ብር) እንዲረዱ አድርገናል፡፡

3ኛ. ለአብነት መምህራን የድጎማ ደመወዝ

ለ12 /አስራ ሁለት/ የአብነት መምህራን በአሉበት ቁጭ ብለው እንዲያስተምሩ ለማድረግ 26,000.00 (ሃያ ስድስት ሺህ) ብር ከፍለናል፡፡

4ኛ. መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሚማሩ መምህራን

ለ40 /አርባ/ መምህራን ወርሃዊ ክፍያ 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር) የተከፈለ ሲሆን ለ3 ዓመት ተምረው ይመረቃሉ፡፡ 



5ኛ. ለተደራጁ ማህበራት የተደረገ ድጋፍ

ለ11 /አስራ አንድ/ ተቋቋሚ ማህበራት 228,000.00 (ሁለት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ብር) እርዳታ ተደርጎላቸው ተቋቁመዋል፡፡

6ኛ. ለቀለም ተማሪዎች የተደረገ ድጎማ

ለ40 /አርባ/ የቀለም ተማሪዎች ክፍያ 30,200.00 (ሰላሳ ሺህ ሁለት መቶ ብር) ተረድተው ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ተደርጓል፡፡ 


7ኛ. በህክምና ለተረዱ ወገኖች

ለ17 /አስራ ሰባት/ ሰዎች የህክምና ድጋፍ 36,000.00 /ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር/ በመለገስ እንዲታከሙ ተደርጓል፡፡



8ኛ. በትራንስፖርት የተረዱ

ለ21 /ሃያ አንድ/ ሰዎች ወደየአካባቢያቸው እንዲመለሱ የተደረገ ድጋፍ 22,000.00 /ሃያ ሁለት ሺህ ብር/ እርዳታ ተደርጓል፡፡

9ኛ. ለኮንዶሚኒየም ቤት የተደረገ ድጋፍ

ኮንዶሚኒየም ቤት ደርሶአቸው ለተቸገሩ ወገኖች የተደረገ ድጋፍ 8,500.00 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) እርዳታ ተደርጓል፡፡

10ኛ. ለጊዜያዊ ተረጂዎች የተደረገ ድጋፍ

ለ150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ ሰዎች የተለያዩ ችግር ገጥሞአቸው ማመልከቻ ላቀረቡና ሠርጋቸውን ላደረጉ ሙሽሮች ቀለበት መግዣ እርዳታ የተደረገላቸው በብር 114,000.00 (አንድ መቶ አስራ አራት ሺህ ብር) ተረድተዋል፡፡ 


11ኛ. ለዓመት በዓል ድጎማ የተደረገላቸው

ለ252 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት/ ሰዎች በታላላቅ ዓመት በዓል ዶሮ መግዣ በማመልከቻ ለጠየቁ ደካማ አረጋውያን ሕመምተኞች 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ ብር) ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

12ኛ. የአትርሱኝ በጾም ጊዜ

ለ121 አባቶችና በገዳም ለሚኖሩ እናቶች በማቴሪያል ሽንብራ፣ ጧፍ፣ እጣንና ሻማ ገዝቶ ለማድረስ 48,000.00 /አርባ ስምንት ሺህ ብር/ ወጪ ሆኖ ታድሏል፡፡

13ኛ. የነዳያን ግብዣ

በዓመት 4 ጊዜ ለአዲስ ዓመት፣ ለገና፣ ለትንሳኤና ለሐምሌ 7 ሥላሴ የምሳ ግብዣ ተዘጋጅቶ ለመጋበዝ 201,000.00 (ሁለት መቶ አንድ ሺህ ብር) በማውጣት የምሳ ግብዣ ተደርጓል፡፡ 



14. ለቤት እድሳት

ቤታቸው ለፈረሰባቸው ሰዎች መልሶ ለመጠገን የተደረገ ድጋፍ 24,000.00 /ሃያ አራት ሺህ ብር/ ተረድተዋል፡፡

15ኛ. ለመጽሐፍ ሕትመትና ለቪዲዮ ቀረጻ

ለሕዝቡ ጠቃሚ የሆኑ መጽሐፍት መጽሔት፣ ቪሲዲ፣ አዘጋጅቶ ለማቅረብ የወጣ ገንዘብ 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ወጪ በማድረግ ታትመዋል፡፡

16ኛ. ለቦንድ ግዢ

በተለያየ ጊዜ ለሀገራችን ለአባይ ግድብ ከወለድ ነፃ የገዛናቸው ቦንዶች 16,000.00 /አስራ ስድስት ሺህ ብር/ ጠቅላላ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ከተለያዩ በጎ አድራጊዎች ገቢ ሆኖ በሥራ ላይ የዋለ ብር ድምር 6,327,727.00 (ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ሰባት ብር) ይሆናል እግዚአብሔር ይመስገን፡፡  

ይህ ሂሳብ የማኅበሩን ገቢና ወጪ አይጨምርም፡፡ እርሱ ለብቻው በውጪ ኦዲተር በየዓመቱ የሚሰራ ነው፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር ሆናችሁ የጽድቅ ሥራ ለሰራችሁ አስራታችሁን ላወጣችሁ በተረጂዎቹ ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡

ሪፖርት አቅራቢ

ሊቀ ትጉ. መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል

የማኅበሩ መስራችና የበላይ ጠባቂ የጠ.ጉባኤ አፈጉባኤ

No comments:

Post a Comment