Monday, July 23, 2018

የዕማማ አመታዊ የጠቅላላ ጉባኤውን ስብሰባ አከናወነ

            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ዛሬ ሀምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም  የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀረበ ሲሆን እንደተለመደው ፕሮግራሙ በጸሎት ከተከፈተ ቡኃላ የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራችና የበናይ ጠባቂ በሆኑት በሊቀ ትጉሃን መምህር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ ቡኃላ በቀትታ በእለቱ ሊከናወኑ ወደታቀዱት ፕሮግራሞች መላትመ
በአመቱ የተከናወኑ አጠቃላይ የስራ ክንውን ሪፖርት ማቅረብ
በውጭ ኦዲተር የተከናወነ የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት በውጭ ኦዲተር ማቅረብ
ለ2011 ዓ.ም እቅድና በጀት ማቅረብና በጠቅላላ ጉባኤው ማጸደቅ
ላለፉት 5 ዓመታት ያገለገሉትን የቦርድ አባላት በክብር ማሰናበትና አዲስ ማስመረጥ ሲሆን

ፕሮግራሙ በታቀደለት ሰአት እንዲከናወን ለማድረግ ተችሎአል ፡፡ በወቅቱም የማህበሩ ስራአስኪያጅ እንደገለጹት በአመት ውስጥ ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በጥቂቱ ከ110 በላይ ሰባኪያንና ዘማሪያንን በመጠቀም በተላያዩ አህጉረ ስብከቶች ላይ ቃለ እግዚአብሄር እንዲሰበክ ተደርጎአል ፡ለበርካታ አቢያተ ቤተ ክርስቲያን ጧፍ እጣን ሻማ እንዲሁም ሙሉ አልባሳት ማደል ፡ ወጣቶችንና አባቶችን በመንፈሳዊ ኮሎጅ ማስተማርና ማስመረቅ የመሳሰሉት ይገኙበታል

Saturday, July 14, 2018

የነዳያን ምሳ ግብዣ ተከናወነ


ዛሬ ሀምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም የአብርሃሙ ስላሴን ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በሊቀ ትጉሃን መምህር ገብረ መስቀል የሚመራው ማህበር በምዕራፈ ቅዱሳን የሰገነት በሕታዊት ኪዳነ ምህረት ቤተ ጸሎት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የነዳያን ምሳ ግብዣ አከናወነ 


ከፎቶ ማህደር