Thursday, November 15, 2018

ፈውስ በማን ነው?

 
ክፍል አንድ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ዘጸ. 15--27
ቃሉን የተናገረው አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት በግልጽ ማስረዳት ነው፡፡ ትእዛዙን ብታደምጥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ በግብፃዊያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ፈውስ የሚለው ቃል ከበሽታ መዳን ጤናን ማግኘት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህዝብ ካለ በበሽታ ሊቀጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‹‹ባትሰሙኝ ትእዛዜን ሁሉ ባታደርጉ ሥርዓቴንም ብትንቁ፣ ፍርሐትን፣ ክሳትንም፣ ዓይናችሁንም የሚያፈዝ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ይላል›› ዘሌዋ. 2614--16
ትእዛዙን የሚጠብቅ ካለግንህማም ሁሉ ካንተ ይርቃል የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ ባንተ ላይ አይደርስብህም ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ዘዳ. 7--15
በሽታ በተለያየ መንገድ ሊከሰት ይችላል፡፡ ንፅህናን ባለመጠበቅ ሊመጣ ይችላል፡፡ እራስን ለእግዚአብሔር ባለማስገዛትም ሊመጣ ይችላል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በበሽታ ከተቀጡ መካከል ስንመለከት፤-
1.እህተ ሙሴ ማርያም እግዚአብሔር ባከበረው በነብዩ ሙሴ ላይ የማይገባትን በመናገሯ እግዚአብሔርንም ባለመፍራቷ በለምጽ ተመትታለች፡፡ ዘኁል. 12-10
2.ነብየ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ ኤልሳ እየዋሸ የማይገባውን ንብረት በመውሰዱ የንዕማንን ለምፅ በዘሩ ላይ ተጣብቆበት የኖረ እንደበረዶም ለምጻም የሆነ ጊያዝን እንመልከት፡፡ 2ኛነገ. 5--25-27
3.የቤተመቅደሱ አገልጋይ ካህኑ ዘካርያስ የእግዚአብሔርን መልክተኛ ባለመታዘዙ 275 ቀናት በላይ ድዳ ሆኖ ተቀጥቷል፡፡ ሉቃ. 1--20
4.ሰርግዮስ የተባለ አገረ ገዥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በፈለገ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይ አገረ ገዥውን እንዳያምን የእግዚአብሔርንም ቃል እንዳይሰማ ጳውሎስንና በርባናስን ተቃወማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳውል የተባለ ጳውሎስ ተንኮል፣ ክፋት የሞላብህ የጽድቅም ጠላት ስለሆንክ ዓይንህ አይይ አለው፡፡ ዓይኑም ታወረ ጽድቅን በመቃወሙ ታመመ፡፡ ሐዋ. 13-- 11