Thursday, August 30, 2018

የሥራ ክንውን መረጃ

   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማኅበር መስራችና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ትጉ. መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል አስተባባሪነትና መሪነት ሰጪዎችንና ተቀባዮችን በማገናኘት በገንዘብና በማቴሪያል ለገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት እንዲሁም ለችግረኛ ወገኖች የተሰጠው ድጋፍ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል የ2009 እና የ2010 ዓ.ም የሥራ ክንውን ሪፖርት በአጭሩ እናቀርባለን፡፡


1ኛ. የአብያተክርስቲያናትና የገዳማት ድጋፍ

በሀገረ ስብከት፣ በወረዳ፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ደብዳቤ ጽፈው ለጽ/ቤታችን ጥያቄ ለአቀረቡ ሁሉ በየተራቸው ለማስተናገድ ሞክረናል፡፡ በዚህም መሠረት በ2009 ዓ.ም በ23 /ሃያ ሶስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ167 /አንድ መቶ ስልሳ ሰባት/ የገጠር አብያተክርስቲያናትና ገዳማት በ2010 ዓ.ም በ16 /አስራ ስድስት/ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ለ102 /ለአንድ መቶ ሁለት/ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት 5,000,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር) በህጋዊ ደረሰኝ እንዲረዱ አድርገናል፡፡ 



2ኛ. በንዋየ ቅድሳት የተረዱ

ለ10,098 /ለአስር ሺህ ዘጠና ስምንት/ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት በጧፍ፣ በእጣን፣ በሻማ፣ በዘቢብ፣፣ በአልባሳት፣ በመጎናጸፊያ፣ በጃንጥላ ወዘተ ለመርዳት የወጣው በገንዘብ ሲተመን ብር 216,027.00 (ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሃያ ሰባት ብር) እንዲረዱ አድርገናል፡፡

3ኛ. ለአብነት መምህራን የድጎማ ደመወዝ

ለ12 /አስራ ሁለት/ የአብነት መምህራን በአሉበት ቁጭ ብለው እንዲያስተምሩ ለማድረግ 26,000.00 (ሃያ ስድስት ሺህ) ብር ከፍለናል፡፡

4ኛ. መንፈሳዊ ኮሌጅ ለሚማሩ መምህራን

ለ40 /አርባ/ መምህራን ወርሃዊ ክፍያ 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር) የተከፈለ ሲሆን ለ3 ዓመት ተምረው ይመረቃሉ፡፡ 

Tuesday, August 21, 2018

የቅኔ ትንቢት ‹‹ሱ››



ቅ/ሥላሴን አንግሱ እንድትወደሱ በመቅደሱ፤
ቅዳሴው ውዳሴው እንዲያርግ ወደእርሱ፤
በጣም ደስይላል የተስተካከለው መቅደሱ፤
ይህንን ለማየት ያዘናችሁ አሁን ደስይበላችሁ በእርሱ፤
በጣም ያምራል የወደፊት መቅደሱ በእርሱ፤
በሀገር መውደድ ገስግሱ እንዳትልከሰከሱ፤
በሃይማት ቁሙ በዘላለም ሕይወት እንድትቀደሱ፤
የሥላሴን ሚስጢር አወድሱ  እንዲመሰገን በመቅደሱ፤
ቅዳሴው ይሰምራል ሲጸዳ መቅደሱ በእርሱ፤
በፍቅር መንገድ ገስግሱ ከላይ ነው እርሱ፤
እንዲሸነፍ ጠላታችን በሃይማት ጎልምሱ፤
              አሁን ጥሩነው የሃይማኖት መቅደሱ አንድ ሆነ በእርሱ፤
              የቀራችሁም ተመልሳችሁ ተቀደሱ በእርሱ፤
              ፀሐይ ይወጣል በመቅደሱ እንድትታደሱ፤
              ሀገር ይስተካከላል በመጥረጊያ ንፋሱ እንዳትተራመሱ፤
              ምእመናን እግዚአብሔርን አንግሱ በመቅደሱ ፤
                                                     ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም
                                                  ከእግዚአብሔር ባሪያና አገልጋይ
                                                 ከሊቀ ትጉ መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል ቀጨኔ

Friday, August 10, 2018

‹‹ቼ››

https://www.facebook.com/MahibereKidaneMihrete/videos/449300138916958/



የቅኔ ትንቢት

እኔ እግዚአብሔር ነኝ ፈጣሪያችሁ አለሁላችሁ ልጆቼ፤

ምነው ተቅበዘበዛችሁ ሕዝቦቼ ተመለሱ ከአምቼ፤

የሰሜኑ ሠራዊቶቼ እንዴትናችሁ ወሬ ሰምቼ ተመለሱ እስከመቼ፤

የአዲሱ ዘመን ነፋሱ አይጠራም ድብልቅልቅ ነው ቅዝቃዜና ሙቀቱ ተጠንቀቁ ወገኖቼ፤

አመለኛ በቅሎ ገዝቼ እየደነበረች አስቸገረች ከአምቼ፤

አይዞሽ ኢትዮጵያ አጥብቀን ከጸለይን ከዘረኝነት የጸዳ ፀሐይ ይወጣል ዘመዶቼ፤

በቤተክህነት አባቶቼ በቤተመንግስት ባለስልጣኖቼ

የተጠራችሁ አላችሁ ተዘጋጁ ወገኖቼ፤

/ት.አሞጽ ም.3 ቁ.7-8/ እግዚአብሔር ከተናገረ የማይናገር የለም፡፡

                                ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም

                                  ከእግዚአብሔር ባሪያና አገልጋይ

                           ከሊቀ ትጉ መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል 

ቪዲዮን ለማግኘት ይጫኑ