Saturday, June 09, 2018

እውነት ወይም ውሸት ብለው ይመልሱ


በሊቀ ትጉ. ባሕታዊ ገ/መስቀል ኃ/መስቀል ላይ ያደረ እግዚአብሔር ያናገራቸውን የትንቢት መልእክቶች ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ ያለውን ዋና ዋናዎቹን መልዕክቶች እናስታውሳችሁ፡፡
1.         ደርግ ኢሰፓ 1983 ዓ.ም አይዘልም ብለው እንደተናገሩት ተፈጸመ፡፡
2.         አራት ኪሎ ሀውልቱ ስር ታላቅ ዘንዶ ይወድቃል ደሙ በከተማ ይፈሳል ደሙን የረገጠ ሁሉ መርዝ  ይሆንበታል ያሉት መንግስቱ መውደቅ ደም ያፈሰሱና ግፍ የሠሩ ሁሉ በመታሰር ተፈጸመ፡፡
3.         አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ የጠዘጋው በር ይከፈታል እልል በሉ፣ ያሉትም ተፈጸመ በሩም ተከፈተ፡፡
4.         በአዲስ አበባ መሀል የቆመው ሐውልት በቅርብ ቀን ይወድቃል፣ በሦስት ሙት ያመኑ ይጠፋሉ ያሉት አፍሪካ አዳራሽ ፊት ለፊት የቆመው የሌኒን ሐውልት ምስል መውደቁ ነው፣ ተፈጸመ፡፡
5.         በአስኮ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ውስጥ ስለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ የነገራቸውን ሲናገሩ አቡነ መርቆረዮስ እና እራደ አንድነት ገዳም ማህበረ ሥላሴ ሄደው ንስሐ ካልገቡ መከራ ይደርስባቸዋልና ምልክቱ በአዲስ አበባ ከተማ እሳት ይነሳል ከፒያሳ በታች ከጎፋ ይጀምራል እርሶም ትልቅ መከራ ይደርስቦታል ይዋረዳሉ ያሉት ተፈጸመ እሳቸውም ተዋረዱ ተሰደዱ እሳቱም በጎፋው ፍንዳታ ተፈጸመ፡፡


6.         ስደት ወደኢትዮጵያ ይሆናል ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ የነፍስ መዳኛ ትሆናለች፣ የተጣላችሁ ታረቁ ንስሐ ግቡ ይሉ ነበር፣ በድንቅነሽ በሉሲ ተፈጸመ፡፡
7.         ለካህናትና ለጳጳሳት እዘኑ አልቅሱ እግዝአብሕር ይፍታ የሚል ካህን እንዳይጠፋ ቤተከርስትያን እንዳይዘጋ እዘኑ እያሉ ይናገሩ ነበር ሲኖዶስ ለሁለት ተከፍሎ በመወጋገዙ የሚታረቅ በመጥፋቱ ቃሉ ተፈጸመ፡፡
8.         በውጣቸውም ያላችሁ ዳኞችና የህዝብ አለቆች በአስቸኳይ ንስሐ ግቡ የቀነ ጅብ ሆናችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር ስማ ስማ ጆሮ ያለው ይስማ ብለው ነበር ተፈጸመ፡፡
9.         ሚያዚያ 7 ቀን 1984 ዓ.ም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ/ክ የተናገሩት ካሉት ጳጳሳት አንድም አይሾምም የሚሾመው እንግዳ ነው ምልክቱ ነጭ ልብስ ይለብሳል ዕድሜ የለውም ብለው ነበር በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተፈጸመ፡፡
10.    ገ/መስቀል በጠመንጃ አፈሙዝ የሚመኩ ይወድቃሉ ብለህ ተናገር  ከሰማይ ምልክት ይታያል ያሉት በቀጨኔ መድሃኒዓለም መጋቢት 30 ቀን የኢትዮጵያ ባንዲራ በሰማይ ላይ 30 ደቂቃ ታይቷል፡፡
11.    ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይመኖት ለተለያችሁ ክርስትያኖች በሙሉ የሚነናደፍ እባብ የሚየስፈራ ጨለማ እልክባችኋለሁ እርስ በእርሳችሁ ትነካከሳላችሁ ተብላችኋል ስማ ስማ ጆሮ ያለው ይማ ፡፡
12.    በአቦል መጽሔት ላይ በቤተመንግሥትና በቤተክህነት ሀዘን ይሆናል ሐምሌንና ነሐሴን አትዘሉም ብለው የተናገሩት በ2004 ዓ.ም በአቶ መለስ ዜናዊና በብፁእ አቡነ ጳውሎስ ሞት ተፈጸመ፡፡
13.    በሃይማኖት ምክንያት ብዙ ፈተና ይደረስብሃል አሥራ አምስት ጊዜ ታስረህ ትፈታለህ የደርግ መንግስት ከ1983 ዓ.ም አይዘልም ብለህ ተናገር አይዞህ ያላቸው ተፈጸመ፡፡
14.    በኢትዮጵየና በኤርትራ መካከል ጦርነት ይነሳል ደም ይፈሳል እሳት አደጋ የማያጠፋው እሳት ኤረትራ ይነሳል፣ እግዚኦ በሉ ይህም በ1990 ዓ.ም ይፈጸማል ብለው ነበር ትንቢቱም በባድሜ ምክንያት ተፈጸመ፡፡
እንግዲህ ከብዙ ትንቢቶቻቸው በጥቂቱ እነዚህን ከሕይወት ታሪካቸው ላይ ወስደን ልከንላችኋል፣ ነገር ግን ሙሉውን ከገጽ 69 ጀምረችሁ አንብቡት፡፡ የ2009 ነሐሴ 3 እና 4 ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡፡
ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም
የቅኔ መልእከት
የ2010 ዓ.ም ዋይታ
Ø  ለባለስልጣኖችና ለሀብታሞች የማትሆን ክፉ ቀን መጣች ዘመነ ማርቆስ እስኪ ተዘገጁ በየላችሁበት
Ø  እር በእርስ ሆነ ግጭትና ጎራ ፣ãረ ለምን ይሆን ይህ ሁሉ መከራ፣
Ø  ከፋፍለው ከፋፍለው ክልል ክልሉን፣እንዴት ይመልሱት አልጋና ዘውዱን፣
Ø  የጠሉሽ ይፈሩ የወደዱሽ ያብሩ አንቺነሽ ኢትዮጵያ የሁሉ መመሪያ፣
Ø  አሞራ በሰማይ ሲበር በክንፉ፣ ተመትቶ ወደቀ ሲያሴር በኢትዮጵያ ላይ፣
Ø  ምነው ጭንቅ ጭን ቅ አለኝ አራቱ ሱባኤ ሲፈጸም ብሔራዊ ሸንጎ ሊገላግለኝ ነው መሰለኝ ፡፡

ነሐሴ 4 ቀን 2009 ዓ.ም
ሺ- ተመለሺ
            
Ø  ገበረመንፈስ ቀዱስ መናኙ መነኩሴ ይዞልሽ ደረሰ አልጋና ዘውድሽን ኢትዮጵያ ተቀበይ ይኸው መጣልሽ ደስ ይበልሽ፣
Ø  ዘውድነሽ ተነሺ እንባሽን አብሺ፣ ሰባት አመት መጣ ገብርዬን አንግሺ፣
Ø  ከብሔር ብሔረሰብሽ ጠቅላይ ሚኒስቴሪሽ ምሁር ይመረጣል በየአምስት አመትሽ፣
Ø  እንግዲህ ይበቃል መከፋፈልሽ አንድነት ሆነልሽ ክፈለ ሀገርሽ፣


                 አሁን በመፈጸም ላይ ያለው ይህ ነው፡፡ እውነት ወይስ ውሽት መልስ ይስጡ፡፡





   



No comments:

Post a Comment