Monday, April 30, 2018

አባታችሁ ርህሩህ እንደሆነ እናንተም ርህሩሆች ሁኑ


አባታችሁ ርህሩህ እንደሆነ እናንተም ርህሩሆች ሁኑ አሥራ በኩራት በ ማውጣት ከዕለት ጉርስ ከአመት ልብስ በመቀነስ መርዳት የነፍስ ዋስትና ነው እንግዲህ በማህበራችን ይጠቀሙ ለአንድ አልጋ ቁራኛ ወይም ለአንድ ሕፃን በየወሩ ለመርዳት 300 ብር እና ለነዳያን ግብዣ በአመት 4ጊዜ ለመጋበዝ የገንዘብ መላኪያ ሒሣብ ቁጥር 
 1ኛ በንግድ ባንክ 1000228290959 
 2ኛ በአዋሽ ባንክ  013220097038200
ብለው ይላኩ ለገጠር ቤተ ክ እና ለልዩ ጉባኤ ማዘጋጃ ድጋፍ ለምታደርጉ በቡና ባንክ 2519501000082 መ/ር ገብረ መስቀል ኃ/መስቀል እያላችሁ መላክ የምትችሉ መሆኘኑን በአክብርት እየገለጽሁ እኔና ኮሚቴውም የታዘዝንውን እንፈጽማለን።

ፍቅር....

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:4-8 - 1 Corinthians 13:4-8
ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር... ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።
Charity suffereth long, and is kind; charity envieth not; charity vaunteth not itself, is not puffed up, Doth not behave itself unseemly, seeketh not her own, is not easily provoked, thinketh no evil; Rejoiceth not in iniquity, but rejoiceth in the truth; Beareth all things, believeth all things, hopeth all things, endureth all things.Charity never faileth: but whether there be prophecies, they shall fail; whether there be tongues, they shall cease; whether there be knowledge, it shall vanish away.

የታላቁ የዋልድባ ገዳም ጥናታዊ ፊልም

YEMM Menefesawi Guzo ….ክፍል 35


ለተከበራችሁ ተመልካቾቻችን የተለያዩ ስብከቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች በዩቲዩብ እየለቀቅን ስለሆነ ከዚህ በታች ያለውን "YouTube" በመጫን Subscribe በማድረግ ይከታተሉን::

ልጆች ሆይ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ


ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:1-3 - Ephesians 6:1-3
፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። ...
Children, obey your parents in the Lord: for this is right. Honour thy father and mother; which is the first commandment with promise; That it may be well with thee, and thou mayest live long on the earth.

Saturday, April 28, 2018

ጥያቄዎቻችሁና መልሶቻቸው

E.O.T.C/YEMM Sibket/ Me. G/meskel….ክፍል 14

ለተከበራችሁ ተመልካቾቻችን የተለያዩ ስብከቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች በዩቲዩብ እየለቀቅን ስለሆነ ከዚህ በታች ያለውን "YouTube" በመጫን Subscribe በማድረግ ይከታተሉን::

የወደቁትን አንሱ

YEMM Menefesawi Guzo ….ክፍል 28

ለተከበራችሁ ተመልካቾቻችን የተለያዩ ስብከቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች በዩቲዩብ እየለቀቅን ስለሆነ ከዚህ በታች ያለውን "YouTube" በመጫን Subscribe በማድረግ ይከታተሉን::

Friday, April 27, 2018

የነዳያን የምሳ ግብዣ ተከናወነ


መንፈሳዊ ዜና እናቀርባለን ውድ ወገኖቻችን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትሳኤውን ምክንያት በማድረግ ሚያዚያ 1 ቀን 2010 . በርካታ ቁጥር ያላቸውን ነዳያን በመጋበዝ በማህበሩ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የምሳ ግብዣ ተደርጎአል እግዚአብሔር ይመስገን በጉልበት በማቴሪያል በገንዘብ ለረዳችሁን ሁሉ በነዳያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን የበአል ዝግጅት ኮሚቴው።



 

ሐዋሪያዊ ተልዕኮ

YEMM Menefesawi Guzo ….ክፍል 27

ለተከበራችሁ ተመልካቾቻችን የተለያዩ ስብከቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶች በዩቲዩብ እየለቀቅን ስለሆነ ከዚህ በታች ያለውን "YouTube" በመጫን ይከታተሉን::

አንዱ ለአንዱ ይጸልይ

ውድ የተዋህዶ ልጆች ይችን አጭር መልዕክት አንብቡአት ቅዱስ ያዕቆብ እንዳለ አንዱ ለአንዱ ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች ይላል እናንተ ለእኔ ጸልዩ እኔም ለእናንተ አጸልያለሁ ከዚህ ውጭ በየቦታው መቅበዝበዝ ይቅርባችሁ ለምሳሌ 1ኛ መራኛ የገብረ ክርስቶስ ገዳም አለ ጠበል ፈልቆአል እያላችሁ ዛር ያደረባት ሴት እያስጠነቆላችሁ አትለቁ 2ኛ አዲስ ዓለም ማርያም እማሆይ አሉ እያላችሁ የአጋንት መንፈስ አታስጎትቱ ንግዲህ ስለስንቱ ነጋዴዎች ልንገራችሁ እራሳችሁን ጠብቁ በሃይማኖታችሁ ጽኑ እላለሁ::

Thursday, April 26, 2018

ትምህርተ ሃይማኖት በምዕራፈ ቅዱሳን

ትምህርተ ሃይማኖት በምዕራፈ ቅዱሳን የሰገነት ኪዳነምህረት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ

ዛሬ ሚያዝያ 16,2010 ዓ.ም በማታው መርሐ ግብራችን ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ በቦታው ተገኝተው ቡራኬአቸውን፦በመስጠት አስተምረውናል ደስ ይበላችሁ





የአንድ ቤተ ክ ጉዳይ ላስተዋውቃችሁ

ዛሬ የአንድ ቤተ ጉዳይ ላስተዋውቃችሁ በመናገሻ አካባቢ የኮሎቦ ቼሻየር ደብረ ሲና አርሴማና ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አዲስ የተተከለ ቤተ ክርስያቲያን ጠበሉ ተባርኮ ጣኦቱ ተደምስሶ ሰው መፈወሻ ሆኖአል ደስ ይበላችሁ በትንሽ መቃኞ ስለሆን ቤተ ክኑን ለመስራት ተባበሩ የባን ሒሳብ ቁጥር 1000083688479 ንግድ ባንክ 0909604152 0920744622 መስቀል






ሥርዓተ ምህላ ጸሎት መመሪያ


  1. 150 ዳዊት በማደል ይደገማል፤
  2. የዘወትር ጸሎት በአማርኝ ይደረሰል፤
  3. ወዳሴ ማርያም መልከአ ማርያም መልከአኢየሱስ ይደገማል፤
  4. ተዓምረ ማርያም ይነበብና እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚለው መዝሙር ይባላል፤
  5. አቤቱ ማረን ይቅር በለን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  6. አድህነነ ከማዓቱ ሰውረነ በምህረቱ በእንተ ማርያም ወላዲቱ  6 ጊዜ ይደረሳል፤
  7. ስምአነ አምላክነ ወመድኃኒነ 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  8. ኪራላይሶን 6 ጊዜ ይደረሳል፤
  9. እግዚኦ ማሃሪነ ክርስቶስ  12 ጊዜ ከዕጣን ጋር፤
  10. በዕንተ  ማርያም መሃሪነ ክርስቶስ 12 ጊዜ፤
  11. በዕንተ  ሚካኤል  3ጊዜ፤
  12. በዕንተ  ገብርኤል  3ጊዜ፤
  13. በዕንተ  ሩፋኤል ወ ኡራኤል  3ጊዜ፤
  14. በዕንተ  መላዕክት  3ጊዜ፤
  15. በዕንተ  ነቢያት  3ጊዜ፤
  16. በዕንተ  ሐዋርያት  3ጊዜ፤
  17. 17.   በዕንተ   ጸድቃን  ወቅዱሳን  3ጊዜ፤
  18. በዕንተ  ሰማዕታት ወጊዮርጊስ 3ጊዜ፤
  19. በዕንተ ሕጻናት መሃሪነ ክርስቶስ  3ጊዜ፤
  20. ማዕጠንት ይታጠናል ከላኛው እስከ ታቸኛው ወለል፤
  21. ተንስኡ ለጸሎት በማለት ጸሎታ ወንጌል ይጸለያል አራቱ ወንጌል ይነበባል፤
  22. ቅዱስ ተብሎ የሠርክ ኪዳን ይደረስና ይታረጋል፡፡
  23. የንስሐ መዝሙሮች ይዘመራሉ
  24. የ30 ደቂቃ የወንጌል ስብከት ተሰጥቶ 1 ሰዓት ተኩል ይጠናቀቅና ምዕመናን ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ይደረጋል፡፡

የሠርክ መሃረነአብ ጸሎት መመሪያ

  1. ከቀኑ 10 ሰዓት ካህናት በመሰብሰብ ዳዊት ይደግማሉ፤
  2. የዘወትር ጸሎት በአማረኛ ይደረሳል፤
  3. ውዳሴ ማርያም ይደገማል፤
  4. ተዓምረ ማርያም የዕለቱ ይነበባል፤
  5. በግራና በቀኝ በመሆን የሃረነአብ  ጸሎት ይደረስና እግዚኦ መሃሪነ ክርስቶስ ይደረሳል፤
  6. ጸሎተ ወንጌል ተጸልዮ አንድ ምዕራፍ ወንጌል ይነበባል፤
  7. የሠርክ የኪዳን ጸሎት ተደርሶ ይታረጋል፤
  8. በዘማሪያን አጭር መዝሙር ይዘመራል፤
  9. የዕለቱ ተራኛ ሰበኪ ወንጌል ይሰብካል፤
  10. እንዳቸርነትህ በሚለው  የንስሐ መዝሙር ጉባኤው ይዘጋና ይታረጋል፡፡

የማህበር ህጋዊ እውቅና ሰርተፍኬትና ሌሎች

የሃይማኖት እውቀት ማሰፋፊያ ማህበር እና የቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ በጎ አድራጎት ማህበር ህጋዊ እውቅና ተሰጠን ለመሆኑ ይህንን መረጃ ማንበብና መረዳት ትችላላችሁ እንዲሁም የሊቀ/ትጉ/መ.ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተሰጣቸው ህጋዊ እውቅና በዚሁ መልእከት ውስጥ ሌሎችንም መረጃዎች የምታገኙ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ፡፡
 
 
 

 


 

የመምህር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል ሐዋርያዊ ተልዕኮ

 
 

 
 

ወርሃዊ የልዩ ጉባኤ መርሀግብር

የሃይማኖትዕዉቀትማስፋፊያማህበርየስብከተወንጌልአገልግሎት
ከመጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ምጀምሮየወጣመርሃግብር
1.  በ3 እና በ16በሊቀትጉኃን መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀልየሚመራ
2.  በ5በመ/ር ሹሜመንግስቴየሚመራ
3.  በ7 እና በ23በሊቀህሩያንየማነብርሃንየሚመራ
4.  በ12መልአከፀሐይቆሞስአባተክለሃይማኖትፀጋዬየሚመራ
5.  በ21በመ/ርዳንኤልአዳሙየሚመራ
6.  በ28 በመ/ር ፍሬቅዱሳንመንክርጥያቄናመልስ
7.  በ29 በመ/ር ገ/ኪዳንከበደየሚመራይሆናል፡፡
ሳምንታዊየሰባክያነወንጌልፕሮግራም
ወርሃዊፕሮግራሙእንዳለሆኖየሳምንቱፕሮግራምእንደሚከተለውይሆናል
በጠዋቱመርሀግብር
1.  መ/ር ዳንኤልአዳሙረቡዕጠዋት
2.  መ/ር ሹምዬመንግስቴሐሙስጠዋት
3.  መ/ር መሪጌታፍሬቅዱሳንአርብጠዋት
4.  መ/ር ገብረኪዳንከበደቅዳሜጠዋት
5.  መልአከፀሐይቆሞስአባ ተ/ሃይማኖትፀጋዬእሁድጠዋት
በማታውመርሀግብር
1ኛ. ረቡዕማታ መ/ር ገብረኪዳንከበደ
2ኛ. ሐሙስማታመሪጌታፍሬቅዱሳን
3ኛ. አርብማታ መ/ር ሹምዬመንግስቴ
4ኛ. ቅዳሜማታሊቀኅሩያንየማነብርሃንገበየሁ
5ኛ. እሁድማታ ዲ/ን አበበተሾመ
የቄደርጥምቀትሲኖርሊቀያየርየሚችልሲሆንተረኛውመድረክመሪይሆናል፡፡

መልካምአገልግሎት!
መጋቢት


ክርስቲያናዊ ስነ-ምግባር 1

የማቴዎስ ወንጌል 25:31-46 - Matthew 25:31-46
የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ