Saturday, September 22, 2018

መንፈሳዊ ዜና


   ሰላም ጤና ይስጥልኝ ይህ የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር መንፈሳዊ ዜና ነው ዜናውን የሚቀርብላችሁ የማህበር ጽ/ቤት ነው

ቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ ማህበር ለሚያስተምራቸው ለ150 ተማሪዎች ለ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መማሪያ የሚሆን የትምህርት መገልገያ ቁሳቁሶችን አከፋፈለ

   ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
ቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ ማህበር በማህበራዊ እሴቶች ላይ በርካታ ስራ እየሰራ ያለ ሲሆን ለ45 አረጋዊያን በያሉበት ቦታ ወርሀዊ በጀት መድቦ እየጦረ ይገኛል አሁንም የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ምክንያት በማድረግ ለሚያስተምራቸው 150 የቀለም ተማሪዎች ቦርሳ ፤ ደብተር ፤ እስክሪብቶ ፤ እርሳስ ፤ መቅረጫ  እና ማስመሪያ በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ደረጃ መሰረት አከፋፍሏል


            

የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር/የዕማማ የ34ተኛ ዓመት የወንጌል አገልግሎት የምስረታ በዓሉን ሊቃነ ጳጳስና የተለያዩ አድባራት አና ገዳማት  አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሰገነት ባህታዊት ኪዳነ ምህረት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አከበረ እግዚአንሔር ይመስገን

    ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
በዓሉን ያስጀመሩት የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራች እና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ተጉ.መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በ1ኛ ዩሀንስ መልዕክት ም 1 ቁ 5 ላይ ያለውን ሀይለ ቃል እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም በሚለው ሀይለ ቃል በመጠቀም ያለፉትን የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑትን ስራዎች አስታውሰው እንኳን ለ34ተኛ ዓመት በብርሀን ለሚመላለሰው የወንጌል አገልግሎት ጉባኤአችን በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በቀጥታ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ኤጲፋኒዎስ መድረኩን አስረክነዋል፡፡


ብጹዕ አቡነ ኤጲፋኒዎስም በዓሉን አስመልክተው እንደተናገሩት የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራች እና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ተጉ.መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀልን ባለፉት 33ዓመት ውስጥ በርካታ መስዋዕትነት መክፈላቸውን በማውሳት ያላቸውን ስሜት በመግለጽ ምእመኑም ከእርሳቸው ጋር በመሆን ሃይማኖቱን ጠብቆ ለዚህ ፍሬ በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው አመስግነዋል ፡፡
በመቀጠልም ሰፋ ያለ ትምህርት አስተምረው መአዱን ከባረኩ በኋላ የእራ ግብዣ ተከናውኗል በመጨረሻም ልዩ ልዩ አስተያየት ከተሰጠ በኋላ ከምሽቱ 2 ሰዓት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
                                      









የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር/የዕማማ የአትርሱኝ ፕሮግራሙን በመናገሻ አምባ ማርያም ገዳም አከናወነ

ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር ከዚህ ቀደም አዘውትሮ እንደሚያደርገው ለአባቶች አትርሱኝ ወይም በጸሎታችሁ አስቡኝ በሚለው መርሀ ግብሩ መሰረት ምእመኑን በማስተባበር በመናገሻ አምባ ማርያም ገዳም ለመናንያን አባቶችና እናቶች እንዲሁም ለአብነት ተማሪዎች ለሆኑት ከ60 በላይ ጋቢ አበርክተዋል በተጨማሪም ለገዳሙ መዋዕለ ህጻናቱ ት/ቤት  የሚሆን ከ100 ኩንታል በላይ ሲሚንቶ እና ለተማሪዎች ደብተር ፤ እስከሪብቶና ሳሙና የመሳሰሉትን አበርክተዋል 



  የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር/የዕማማ ዓለማቀፍ የስብከት አገልግሎት በማስፋት ምዕመኑ በርቀት ሆኖ ቃለ እግዚአብሔር እንዲማር የሚያስችል ድህረ ገጽ  በስራ ላይ አዋለ

   ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር ከዚህ ቀደም የተለያዩ መህበራዊ ድህረ ገጾች ወይም ሚዲያዎች በአብነትም በዩቲዩብ ፤ በብሎግ እና በፌስቡክ በመጠቀም አለማቀፍ የወንጌል አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የሚያገለግለውን አገልግሎት በማሳደግ ምዕመኑ በርቀት ሆኖ ትምህርት መማር የሚችልበትን ሁኔታ በማመቻቸት ምዕመኑ ምንም ሳይቸገር ባለበት ቦታ ሆኖ ቃለ እግዚአብሔር እንዲማር ጥሪ አቅርቧል፡፡

 የድህረ ገጹ አድራሻ   www.eotcyemm.org
የርቀት ትምህርቱን ለመከታተል http://apps.eotcyemm.org/startlessons.php

  የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር/የዕማማ በሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉና ችግር ለደረሰባቸው እርዳታ አደረገ

   ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር በሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉና ችግር ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ምዕመኑን በማስተባበር  የ 76,000 (ሰባ ስድስት ሺ  ብር ) እርዳታ አድርጓል



1 comment: