Thursday, November 15, 2018

ፈውስ በማን ነው?

 
ክፍል አንድ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው ዘጸ. 15--27
ቃሉን የተናገረው አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ የጽሑፉ ዋና ዓላማ የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት በግልጽ ማስረዳት ነው፡፡ ትእዛዙን ብታደምጥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ በግብፃዊያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ፈውስ የሚለው ቃል ከበሽታ መዳን ጤናን ማግኘት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የማይታዘዝ ህዝብ ካለ በበሽታ ሊቀጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‹‹ባትሰሙኝ ትእዛዜን ሁሉ ባታደርጉ ሥርዓቴንም ብትንቁ፣ ፍርሐትን፣ ክሳትንም፣ ዓይናችሁንም የሚያፈዝ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ ይላል›› ዘሌዋ. 2614--16
ትእዛዙን የሚጠብቅ ካለግንህማም ሁሉ ካንተ ይርቃል የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ ባንተ ላይ አይደርስብህም ብሎ ለሙሴ ነግሮታል፡፡ ዘዳ. 7--15
በሽታ በተለያየ መንገድ ሊከሰት ይችላል፡፡ ንፅህናን ባለመጠበቅ ሊመጣ ይችላል፡፡ እራስን ለእግዚአብሔር ባለማስገዛትም ሊመጣ ይችላል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ በበሽታ ከተቀጡ መካከል ስንመለከት፤-
1.እህተ ሙሴ ማርያም እግዚአብሔር ባከበረው በነብዩ ሙሴ ላይ የማይገባትን በመናገሯ እግዚአብሔርንም ባለመፍራቷ በለምጽ ተመትታለች፡፡ ዘኁል. 12-10
2.ነብየ እግዚአብሔርን ባለመታዘዙ ኤልሳ እየዋሸ የማይገባውን ንብረት በመውሰዱ የንዕማንን ለምፅ በዘሩ ላይ ተጣብቆበት የኖረ እንደበረዶም ለምጻም የሆነ ጊያዝን እንመልከት፡፡ 2ኛነገ. 5--25-27
3.የቤተመቅደሱ አገልጋይ ካህኑ ዘካርያስ የእግዚአብሔርን መልክተኛ ባለመታዘዙ 275 ቀናት በላይ ድዳ ሆኖ ተቀጥቷል፡፡ ሉቃ. 1--20
4.ሰርግዮስ የተባለ አገረ ገዥ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በፈለገ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይ አገረ ገዥውን እንዳያምን የእግዚአብሔርንም ቃል እንዳይሰማ ጳውሎስንና በርባናስን ተቃወማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሳውል የተባለ ጳውሎስ ተንኮል፣ ክፋት የሞላብህ የጽድቅም ጠላት ስለሆንክ ዓይንህ አይይ አለው፡፡ ዓይኑም ታወረ ጽድቅን በመቃወሙ ታመመ፡፡ ሐዋ. 13-- 11

Wednesday, September 26, 2018

ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ

ወገብረ ሰላመ  በደመ  መስቀሉ <<በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን አደረገ>> ቆላ. 1-፡-20

 

መስቀል በቀደመ ዘመን ለኃጢአተኞች እግዚአብሔርን ለበደሉ መቅጫ የነበረ ነው፡፡ በእንጨት ላይ የተሰቀለም በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፡፡ ኦ/ዘዳ 21፡23 በሐዲስ ኪዳን ግን ለክርስቲያኖች ኃይል  ጽንዕ ቤዛና መድኃኒተ ነፍስ ሆኖ የሚያገለግል ዓርማ ነው፡፡ መስቀል የምንለው በቁሙ ከቤተክርስቲያን ጉልላት እስከ ምዕመናን ንቅሳት የሚታይ የድል ምልክት የደህንነት ዓርማ (ምልክት) የክርስቲያኖች የማንነት መገለጫ    የተጋድሎ ፍኖት ነው፡፡ 1ጴጥ. 2፡21                          
የክርስቶስ  መስቀል ለምናምን  ለኛ  ፡- የጥል ግድግዳ የፈረሰበት  ሰላማችን ነው  ኤፌ 2፡14 ሰው እንጨት ቆርጦ ቢበላ አምላኩን በደለ የፀብ ግድግዳም ተተከለ  ሰው ከአምላኩ ተለየ፡፡ ‹‹ለያይቶን የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰና አይሁዳዊያንና አሕዛብን አንድ ያደረገ ሰላማችን ክርስቶስ ነው›› እንዲል: : ከእርሱ ጋር የታረቅንበት ኃይላችን ነው በመስቀል ላይ በመሞት ጠላትን አስወገደ ሁለቱንም አንድ አካል አድርጎ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ እንዲል ኤፌ. 2፡16 ጠላታችን የራቀበት እኛ የቀረብንበት ጋሻችን ነው፡፡ የቀደመው እባብ የዲያብሎስን ራስ የተቀጠቀበት እኛም ድል መንሳትን በግለጥ ያየንበት  ዕፀ መድኃኒት ነው፡፡ በእኛ የነበረውን የሚቃወመንንም በትዕዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ደበዳቤ ፅሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀሉ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው እንዲል ቆላ. 2፡14 ዐረፍተ ማዕከል የተናደበት የሕይወት ህብስት የተቆረሰበት ዕፀ መስቀል በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት በዓለ መስቀልን መከበር የተጀመረው ዛሬም በኢትዮጵያችንም በተለይ በግሸን ደብረ ከርቤ  ከአራቱ ማዕዘን በሚመጡ ምዕመናን በደማቅ ሁኔታ  እየተከበረ ይገኛል:: መስቀል በዓመት አምስት ጊዜ የሚከበር ሲሆን ይኸውም መስከረም 16 ቀን የደመራ በዓል ቅዳሴ ቤት መስከረም 17 ቀን ንግስት ዕሌኒ ቁፋሮ ያስጀመረችበት መስከረም 10 ቀን አፄ ዳዊት መስቀሉን የተረከቡበት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገቡበት ተቀፀል ጽጌ ይባላል፡፡ መስከረም 21 ቀን 1446 ዓ.ም በግሸን ተራራ ያረፈበት በማስመልከት በየዓመቱ  እየታሰበ ይገኛል፡፡   በረከተ መስቀሉ  አይለየን!     

አድራሻ፡- ከቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ/ክ ዝቅ ብሎ ያገኙናል
በም.ቅዱ.የሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተ ጸሎት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ፡- 0911-877059 / 0111-572581 / 0920-744622 ጉ/ክ/ከተማ አ.አ. ኢትዮጵያ

Saturday, September 22, 2018

መንፈሳዊ ዜና


   ሰላም ጤና ይስጥልኝ ይህ የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር መንፈሳዊ ዜና ነው ዜናውን የሚቀርብላችሁ የማህበር ጽ/ቤት ነው

ቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ ማህበር ለሚያስተምራቸው ለ150 ተማሪዎች ለ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መማሪያ የሚሆን የትምህርት መገልገያ ቁሳቁሶችን አከፋፈለ

   ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
ቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ ማህበር በማህበራዊ እሴቶች ላይ በርካታ ስራ እየሰራ ያለ ሲሆን ለ45 አረጋዊያን በያሉበት ቦታ ወርሀዊ በጀት መድቦ እየጦረ ይገኛል አሁንም የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ምክንያት በማድረግ ለሚያስተምራቸው 150 የቀለም ተማሪዎች ቦርሳ ፤ ደብተር ፤ እስክሪብቶ ፤ እርሳስ ፤ መቅረጫ  እና ማስመሪያ በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ደረጃ መሰረት አከፋፍሏል


            

የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር/የዕማማ የ34ተኛ ዓመት የወንጌል አገልግሎት የምስረታ በዓሉን ሊቃነ ጳጳስና የተለያዩ አድባራት አና ገዳማት  አስተዳዳሪዎች በተገኙበት በሰገነት ባህታዊት ኪዳነ ምህረት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አከበረ እግዚአንሔር ይመስገን

    ዝርዝሩም  ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል
በዓሉን ያስጀመሩት የሃይማኖት እውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራች እና የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ተጉ.መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በ1ኛ ዩሀንስ መልዕክት ም 1 ቁ 5 ላይ ያለውን ሀይለ ቃል እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም በሚለው ሀይለ ቃል በመጠቀም ያለፉትን የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑትን ስራዎች አስታውሰው እንኳን ለ34ተኛ ዓመት በብርሀን ለሚመላለሰው የወንጌል አገልግሎት ጉባኤአችን በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልእክት ካስተላለፉ በኋላ በቀጥታ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ኤጲፋኒዎስ መድረኩን አስረክነዋል፡፡

የተፈጸሙ የትንቢት መልዕክቶች


          4ኛ እትም በሚለው መጽሐፍ ላይ ይመልከቱ ከ1977-2010 ዓ.ም

      1. በገጽ 9 እና 22 ይታደስ ቤታችን ይደግ ከተማችን  የመናገሻው አንባችን ለሁላችን          እንፍታው ተባብረን ያለ ችግራችን (በአዲስ አበባ ከተማችን ተፈጸመ)
     2. የቡናው አዝመራ ሲታይ በሀገራችን እርሱ ነው የውጭ ገቢያችን የሸማኔው ሥራ             ሲታይ በጓሮአችን ጨምሯል ምርታችን (በገበያውና በውጭ ምንዛሪ ተፈጸመ)
      3. በገጽ 24 ደርግ ኢሰፓ 1983 . አይዘልም ንስሐ ግቡ ያሉት ተፈጸመ
       አራት ኪሎ ሀውልት ስር ታላቅ ዘንዶ ይወድቃል ደሙም በከተማ ይፈሳል ደሙን             የረገጠ ሁሉ መርዝ ይሆንበታል ያሉት በደርግ ሹማምንት ተፈጸመ
    4. በገጽ 26 ለጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ጳጳሳትና ካሕናት እዘኑ አልቅሱ              ቤተክርስትያን እንዳትዘጋ በማለት ተናግረው ነበር፤ በአስኮ ገብርኤል ለፓትርያርኩ የነገሩአቸው መልእክት አቡነ መርቆርዮስና እራደ አንድነት ገዳም ማኅበረ ሥላሴ ሄደው ንስሐ ይግቡ ብሎኛል ይህንን ባያደርጉ ከባድ ችግር ይደርስብዎታል ብለዋቸው ነበር ተፈጸመ፤

ስለመመለሳቸው ደግሞ

5   5. በገጽ 22 በአራቱም መአዘን ሁሉንም አንድ አደረግሽ ውሃ ነዳጅ ጨው አለሽ ምን አጥተሸ ለኑሮሽ የተከፈለውን ሃይማትሽን አንድ አድርገሽ ታሸንፊያለሽ ሰብስበሽ ያሉት ተፈጸመ ነዳጁም ወጣ የጠለያየውም አንድ ሆነ፤
6   6. ነገጽ 44 ስለራሳቸው የተናገሩት /መስቀል ጽና በርታ ከጀንበር መጥለቂያ ቀይ ልጃገረድ ተመርጣ ትመጣለች 3 ልጆች ትወልዳለህ ያላቸው ተፈጸመ
7. ስለሁለቱ ጥል በገጽ 30 በትግራይና በኤርትራ መካከል ጦርነት ይነሳል ደም ይፈሳል ያሉት ተፈጸመ  ስለእርቁ ደግሞ
ኮብልዬ ነበረ ከሀገር ተገንጥዬ ተመልሼ መጣሁ ተቀበይኝ ብዬ እንኳን ደህና መጣሽ እምዬ ገላዬ ያሉት ተፈጸመ በገጽ 22 የአስመራውን መንገድ አንድ አደረግሽ እንኳን ደስ አለሽ ይህም ተፈጸመ

ስለአሰብ ወደብ

Saturday, September 15, 2018

የ34ኛ ዓመት የወንጌል አገልግሎት እነሆ

በሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር /ቤት መስከረም 6/2011/
34 ዓመት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጀመረበትን ዓመት
ምክንያት በማድረግ የቀረበ አጭር ታሪክ
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
ይህ መልእክት ለእስራኤል አንድ ጊዜ ተሰጥቶል የቆመ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ከሚነሳው ትውልድ ጋር ሲመላለስ የሚኖር የማያቋርጥ ትምህርት  ወንጌል ሲሆን በየጊዜው ተደጋግሞ ሊነገርም የሚገባው ነው፡፡
በእስራኤል መካከል በግ የሚያረባ ገበሬ ለበጎች ማደሪያ የሚሆን መግቢያውና መውጫው አንድ የሆነ ክብ ሆኖ በድንጋይ የታነጸ ጋጥ (በረት)ያበጁ ነበር፡፡ ፀሐይም መጥለቅ በሚጀመርበት ወቅት እረኛው ለምለም ሣር እያበላ ሲጠብቅ ከዋለበት መስክ የበጉን መንጋ ስብስቦ ወደ ማደሪያቸው ያስገባቸው ነበር፡፡
እረኛው ቀን እንደሚጠብቃቸው ሁሉ አውሬ እንዳይበላቸው ሌባ ሰርቆ እንዳይወስዳቸው ሌሊትም ቢሆን ራሱ ከመንጋው ማደሪያ በር ላይ ተገኝቶ ይጠብቃቸው ነበር፡፡
በትንቢተ ሕዝቅ. .3 16 እንደተባለው የእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ ስለዚህ አንተ ሐጢአተኛውን ሰው ከክፉ መንገድ እንዲመለስ ነግረህ ባታስጠነቅቅውና ባሐጢአቱ ቢሞት ደሙን ከእጅህ እፈልጋለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ነግረኸው ወይም አስተምረኸው ሳይመለስ ቢሞት አንተ ነፍስህን አድነሃልና በሕይወት ትኖራለህ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት እግዚአብሔር ባሕታዊ /መስቀልን አስነስቶ ላከልን እኛም በቃሉ ተማረክን፡፡ 
     እንዲህ ያሉትንም የመንፈስ ረሃብተኞች ከቸሩ እረኛቸው ከክርስቶስ ጋር ልናስተዋውቃቸውና ከማዕድም ተመግበው  እንዲጠግቡ ልናደርጋቸው ታዘናል፡፡ የአውሬውም እራት እንዳይሆኑ ልንጠብቃቸው ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌም እረኛ በጎቹን የለመለመ ሣር እንዲነጩ የጠራ ውኃ እንዲጎነጩ ወደ መስክ የሚያሰማራቸው ከተኩላና ቀበሮ አፍ የሚጠብቃቸው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለበጎቹ ጥቅምና ደኅንነት ጭምር የሚያስብ መሆን አለበት፡፡
      የመንጋው ጠባቂ የሆነው እውነተኛው እረኛችን ክርስቶስ ግን ስለበጎቹ ሕይወቱን ከመሰዋቱም  ሌላ የመንፈስ እረኃብተኞች ለሆነው ሁሉ ሕይወት መድኀኒት የሆነውን ቅዱስ ሥጋውን ዘወትር ይመግበናል፡፡ በመንፈስ ጥም ተይዘን ለምንሰቃየውም ክቡር ደሙን ጠጥተን እንድንረካ ሰጥቶናል ወደ እርሱም የምንመጣውን ወደ ውጭ አያወጣንም፡፡ሰለዚህ ነው ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነውበለመለመ መስክ ያሳድረኛል ወደ እረፍትም ውኃ ይመራኛል ያለው፡፡