Saturday, September 22, 2018

የተፈጸሙ የትንቢት መልዕክቶች


          4ኛ እትም በሚለው መጽሐፍ ላይ ይመልከቱ ከ1977-2010 ዓ.ም

      1. በገጽ 9 እና 22 ይታደስ ቤታችን ይደግ ከተማችን  የመናገሻው አንባችን ለሁላችን          እንፍታው ተባብረን ያለ ችግራችን (በአዲስ አበባ ከተማችን ተፈጸመ)
     2. የቡናው አዝመራ ሲታይ በሀገራችን እርሱ ነው የውጭ ገቢያችን የሸማኔው ሥራ             ሲታይ በጓሮአችን ጨምሯል ምርታችን (በገበያውና በውጭ ምንዛሪ ተፈጸመ)
      3. በገጽ 24 ደርግ ኢሰፓ 1983 . አይዘልም ንስሐ ግቡ ያሉት ተፈጸመ
       አራት ኪሎ ሀውልት ስር ታላቅ ዘንዶ ይወድቃል ደሙም በከተማ ይፈሳል ደሙን             የረገጠ ሁሉ መርዝ ይሆንበታል ያሉት በደርግ ሹማምንት ተፈጸመ
    4. በገጽ 26 ለጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ጳጳሳትና ካሕናት እዘኑ አልቅሱ              ቤተክርስትያን እንዳትዘጋ በማለት ተናግረው ነበር፤ በአስኮ ገብርኤል ለፓትርያርኩ የነገሩአቸው መልእክት አቡነ መርቆርዮስና እራደ አንድነት ገዳም ማኅበረ ሥላሴ ሄደው ንስሐ ይግቡ ብሎኛል ይህንን ባያደርጉ ከባድ ችግር ይደርስብዎታል ብለዋቸው ነበር ተፈጸመ፤

ስለመመለሳቸው ደግሞ

5   5. በገጽ 22 በአራቱም መአዘን ሁሉንም አንድ አደረግሽ ውሃ ነዳጅ ጨው አለሽ ምን አጥተሸ ለኑሮሽ የተከፈለውን ሃይማትሽን አንድ አድርገሽ ታሸንፊያለሽ ሰብስበሽ ያሉት ተፈጸመ ነዳጁም ወጣ የጠለያየውም አንድ ሆነ፤
6   6. ነገጽ 44 ስለራሳቸው የተናገሩት /መስቀል ጽና በርታ ከጀንበር መጥለቂያ ቀይ ልጃገረድ ተመርጣ ትመጣለች 3 ልጆች ትወልዳለህ ያላቸው ተፈጸመ
7. ስለሁለቱ ጥል በገጽ 30 በትግራይና በኤርትራ መካከል ጦርነት ይነሳል ደም ይፈሳል ያሉት ተፈጸመ  ስለእርቁ ደግሞ
ኮብልዬ ነበረ ከሀገር ተገንጥዬ ተመልሼ መጣሁ ተቀበይኝ ብዬ እንኳን ደህና መጣሽ እምዬ ገላዬ ያሉት ተፈጸመ በገጽ 22 የአስመራውን መንገድ አንድ አደረግሽ እንኳን ደስ አለሽ ይህም ተፈጸመ

ስለአሰብ ወደብ

8    8. ስገሪ በቅሎዬ ስገሪ በናትሽ አሰብ ላይ ድረሺ መርከቡ ሲታይሽ ያሉት ተፈጽሞ መርከቡ ሥራ ጀመረ

ስለአባይና ስለሰንደቅ አላማችን

9   9. በገጽ 33 ላይ አባይን ለሙሾ ማን አደረገው በመስኖ ይታያል አመሻሹ ላይ ያሉት ተፈጸመ በገጽ 70 አንድነት ኃይል ነው በኢትዮጵያ ሲታይ እንዴት ያስድታል ያዝመራ ሲሳይ ሰንደቅ ዓላማችን ይውለብለብ በዓለሙ ላይ ትኩሳቱ ጠፍቷል በተራራ ፀሐይ እኛ ደስብሎናል በአባይ ውሃላይ በማለት የተናገሩት ተፈጸመ፤ በገጽ 64 ላይ አባይ ጠየሰ ምንድነው እርሱ ሱሪ ልበሱ ያሉት ተፈጸመ

ስለምስራቁ ሱማሌ እልቂት

10. በገጽ 37 ከምስራቅ ኢትዮጵያ ጭጋግ ያድነን ያሉት በገጽ 31 በምስራቅ ኢትዮጵያ እሳት ይነሳል በገጽ 65 መርዙ  ተሰራጨ ያሉት ተፈጸመ

ስለአንድነት ፓርቲ

1    11. በገጽ 52 ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይመረጥ ለሥራ ፍሬ የአንድነት ፓርቲ ይኑር ለሀገሬ ያሉት ተፈጸመ

ስለዶ/ር አብይ ምርጫ

1     12. በገጽ 21 ደግሞም ይቀጥላል ንጉሥሽ በፍቅር ነው መንገድ ጠራጊሽ እንደራሲሽ ለሰላምሽ ያሉት ተፈጸመ
    በገጽ 76 የታፈነ ነፋስ ሲፈነዳ ቤት ያፈርሳልና ጸልዩ ተብላችኋል ያሉት በድንገት በመሀል ከተማ ፈረሰጮች ይገባሉ ፀሐይም ይወጣል ያሉት ተፈጸመ
በገጽ 78 ከብሔር ብሔረሰብሽ ጠቅላይ ሚኒስቴርሽ ምሁር ይመረጣል ያሉት ተፈጸመ
በገጽ 78 ስለ2011 አዲሱ ዓመት የተናገሩት የአዲሱ ዘመን ነፋሱ አይጠራም ድብልቅልቅ ነው ቅዝቃዜና ሙቀቱ ተጠንቀቁ ወገኖቼ ያሉት በቡራዩ እየተፈጸመ ይገኛል፡፡
       ይህ ሁሉ ገጽ ማውጫ ነው በደንብ ሁሉንም አንብቡት፡፡

No comments:

Post a Comment