Thursday, April 26, 2018

ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤያት

ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤያት
በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀዳሚና ተቀባይነት ያላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም የምትቀበላቸውና ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጭነት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አበይት ጉባኤያት 3 ናቸው፡፡
እነዚህም
1-
ጉባዔ ኒቅያ 325 ዓም
2-
ጉባዔ ቁስጥንጥንያ 381 ዓም እና
3-
ጉባዔ ኤፌሶን 431 ዓም ናቸው፡፡
1) ጉባኤ ኒቅያ (325 .)
የኒቂያ ጉባኤ የተጠራው የአርዮስን ክህደት ለመቃወም ነው፡፡ የአርዮስ ክህደት መነሻ ያደረገው በምሳ. 822 ያለውን ቃል ነው ማለትም ‹‹እግዚአብሔር ዓለማትን ሳይፈጥር አስቀድሞ ፈጠረኝ›› የሚለውን በማንሳት ‹‹ወልድ ፍጡር ነው›› እያለ ማስተማር ጀመረ፡፡ በዚህ አካሄዱ ብዙዎችን ማሳሳት ጀመረ የእስክንድርያ ሊቀጳጳስ አለ እስክንድሮስ ከክህደቱ እንዲመለስ ብዙ ጣሩ ነገር ግን እርሱ ሊመለስ አልቻለም እንደውም 320 ጀምሮ ክህደቱን ማስፋፋት ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ እለ እስክንድርዮስ 100 የሚያህሉ ኤጲስ ቆጶሳትን ሰብስቦ ክህደቱን አስረዳቸው፡፡


ጉባኤውም የአርዮስን ክህደት ከመረመሩ በኋላ አወገዙት ጉዳዩ በእስክንድርያ ብጥብጥና ሁከታን እያስከተለ በመሄዱ ንጉሱ ቆስጠንጢኖስ የስፔንኑን ኤጲስ ቆጶስ ሆስያስን ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ ከኤጲስ ቆጶሳት ጋር ሲወያይ ሰንብቶ ወደ ንጉሱ ተመለሰ፡፡ ጉዳይ በሽምግልና መፍታት እንደማይቻል ለንጉሱ አስረዳው፡፡ ከዚህ በሁዋላ ጉባኤው እንዲደረግ ተወስኗል፡፡
ጉባኤው በአርዮስ ክህደት ላይ ተወያይቶ አርዮስና ተከታዮቹ የወልድን የባህርይ አምላክነት በመቃወም የጠቀሳቸው ጥቅሶች የተሳሳቱ እንደሆኑ አስረድቷል፡፡በዚህም መሠረት በምሳሌ 8÷22 የተጠቀሰው ጥቅስ ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከአብ ባህርይ መገኘቱን (መወለዱን) እንጂ እንደፍጡራን ሁሉ ያልተፈጠረ መሆኑን አርዮስ እንዲረዳው የጉባኤው አባቶች ብዙ ደክመዋል፡፡ ከቅዱሳት መጽሐፍትም ቃል እየጠቀሱ ቃለ እግዚአብሔር ወልድ የባህርይ አምላክ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ወልድ የአብ የባህርይ ልጅ አንጂ ያልተፈጠረ መሆኑን ለማስረዳት የተጠቀሱትም (ዮሐ 1÷1-14 እና 14÷30 ሮሜ 9÷15 1ዮሐ 5÷20) እና እነዚህን የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አርዮስ ከክህደቱ ሊመለስ ባለመቻሉ 318 ቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ ‹‹እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ›› በመሆን አርዮስን አውግዘው የወልድን አምላክነት የሚገልጽ የሃይማኖት አንቀጽ አፀደቁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም 318 ሊቃውንት 325 . በኒቅያ ጉባኤ የተወሰነውን ውሳኔ ተቀብላ ታስተምራለች፡፡
2)
የቁስጥንጥንያ ጉባኤ (381 .)
የቁስጥንጥንያ ጉባኤን የተሰበሰቡት 381 . ነው፡፡ ጉባኤውን የተሰበሰቡበት ምክንያቶች የመቅዶንዮስን፣ የአቡሊናርዮስንና የአውሳብዮስን ክህደቶች በመስማት ነው፡፡
የመቅዶንዮስ ክህደትም የመንፈስ ቅዱስን ከአብና ከወልድ ጋር በባህርይ በመልክ አንድ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ከሰረፀ አብ እና ወልድም መንፈስ ቅዱስን ከላከና መልዕክተኛ ከሆነ ከእርሱ ጋር ትክክል አይደለም ከእነርሱ በታች (ህፁፅ) ነው የሚል ነበር፡፡ ይህ ትምህርቱም በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት መዛመት ስለጀመረ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ኤጲስቆጶሳት በቁስጥንጥንያ 301 . ተሰብስበው ዐቢይ ጉባኤ አደረጉ፡፡ በዚህ ጉባኤ ከብሉያትና ከሐዲሳት እየጠቀሱ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ቢሰርፅም ከአብና ከወልድ ጋር በባህርይ በመለኮት አንድ መሆኑን ከእነርሱ ጋር ትክክል መሆኑን (መዝ. 336 ኢሳ. 63 የሐዋ. 2828) በመጥቀስ ትምህርቱን አውግዘዋል፡፡
በኒቂያ 318 ቅዱሳን አበው የወሰኑትንም አንቀጸ ሃይማኖት በማጠናከር የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት በሚገባ ገልጸው ‹‹ከአብ የሰረፀ ጌታ ሕይወት ሰጭ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን ከአብ እና ከወልድ ጋር እንሰግድለታለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው›› ብለው በኒቂያ የሃይማኖት ውሳኔ ላይ ጨምረው ወሰኑ፡፡
3)
የኤፌሶን ጉባኤ (431 .)
-
ጉባኤ ኤፌሶን 431. በኤፌሶን ከተማ 200 ሊቃውንት የተካሄደ ነው፡፡ የስብሰባው መሪ ቄርሎስ ነበር፡፡
-
የስብሰባው ዋና ምክንያት የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡
-
ንስጥሮስ የተማረው በአንጾክያ ሲሆን ክህደቱም ለክርስቶስ ሁለት ባህሪያት አሉ፡፡ አምላክም ሰው የሆነው በንጽረት ነው፡፡ ንጽረት ማለትም እመቤታችን የወለደችው ሰውን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እርሱአም ወላዲተ አምላክ አትባልም የሚል ነው፡፡
-
ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታውና መልስ ያሳጣው እስክንድርያዊው ሊቀጳጳስ ቄርሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ "የእግዚአብሔር ልጅ በማርያም አደረ፡፡ በመከራም ጊዜ ተለየው" የሚሉ ንስጥሮስንና ወገኖቹን የተጠቀሰውን የማርያም ልጅ ብቻ ከሆነ ጥያቄ በክህደትና በድፍረት የተከፈተ አፋቸውን አስይዞ ይመልሳቸው እንደነበር የቤተክርስቲያን ፀሐፊዎች ዘግበውታል፡፡
ምንጭ፡- የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በከፊል የተወሰደ

3 comments: