Friday, August 10, 2018

‹‹ቼ››

https://www.facebook.com/MahibereKidaneMihrete/videos/449300138916958/



የቅኔ ትንቢት

እኔ እግዚአብሔር ነኝ ፈጣሪያችሁ አለሁላችሁ ልጆቼ፤

ምነው ተቅበዘበዛችሁ ሕዝቦቼ ተመለሱ ከአምቼ፤

የሰሜኑ ሠራዊቶቼ እንዴትናችሁ ወሬ ሰምቼ ተመለሱ እስከመቼ፤

የአዲሱ ዘመን ነፋሱ አይጠራም ድብልቅልቅ ነው ቅዝቃዜና ሙቀቱ ተጠንቀቁ ወገኖቼ፤

አመለኛ በቅሎ ገዝቼ እየደነበረች አስቸገረች ከአምቼ፤

አይዞሽ ኢትዮጵያ አጥብቀን ከጸለይን ከዘረኝነት የጸዳ ፀሐይ ይወጣል ዘመዶቼ፤

በቤተክህነት አባቶቼ በቤተመንግስት ባለስልጣኖቼ

የተጠራችሁ አላችሁ ተዘጋጁ ወገኖቼ፤

/ት.አሞጽ ም.3 ቁ.7-8/ እግዚአብሔር ከተናገረ የማይናገር የለም፡፡

                                ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም

                                  ከእግዚአብሔር ባሪያና አገልጋይ

                           ከሊቀ ትጉ መ/ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል 

ቪዲዮን ለማግኘት ይጫኑ

የእግዚአብሔር ድምጽ



ነሐሴ 2 ቀን 2010 .


የእግዚአብሔር ድምጽ ከተማይቱን ይጠራታል /. ምልክያስ .6 .9/  ኑና የእግዚአብሔርን ቃል እንስማ ቃሉ እነዲህ ይላል /ያዕ..1 .26/  አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው፤ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔርአብ ዘንድ ይህ ነው ወላጆች የሌላቸውን ልጆችና ባልቴቶችን በመከራቸው መጠየቅና መርዳት በዓለም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን በንስሐ መጠበቅ ነው ይላል፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ  ሰው በሃይማኖቱ በመጽናት ንስሐ እየገባ እድፉን በማራቅ የሚኖር ሲሆን ንጹሕ የሆነውን የወገን መርዳት ሥራ እየሠራ እግዚአብሔርን እንደሚያስደስት ይታወቃል ስለዚህ ወገኖቼ በም.. የሰገነት ኪዳነምሕረት ቤተጸሎት የስብከተወንጌል አዳራሽ 1-3 በምህላ ፀሎትና በስብከት 5 7 12 16 21 23 28 እና 29 የጥያቅና መልስ ምክርነት ዝማሬና ስብከት በነዚህ ቀን ጧፍ በማብራት በልዩ ጉባኤ እናከብራለን ይምጡና ይጠቀሙበት፡፡ /ማቴ. .5 1-12/

አድራሻ፡- ቀጨኑ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አጠገብ እንገኛለን

ላልደረሳቸው ያዳርሱ!!!

ለበለጠ መረጃ፡- 0911-877059 /011-572581/ 0920744622

በወር 2 ጊዜ 3 16 ይህቺን በራሪ ወረቀት ያገኛሉ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጉለሌ /ከተማ

ከእ.. /ቤት