ስንኖር
ኢትዮጵያዊ ስንሞት በአፈርዋ ኢትዮጵያ የምንሆንባት ሀገራችን በየሰላሳ 30 አመቱ ብዙ መከራ ሲገጥማት ቆይቶአል አሁንደግሞ በዋዜማው ብዙ ችግር ገጥሙዋታል ምንም እንኩዋን ከተሞች ቢበዙና ፎቆች ቢሰሩ በርካታ እንበርስቲዎችና ት ቤቶች ቢገነቡ በርከታ ግድቦችና መንገዶች ቢሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አልተመለሰም ይላሉ የሀዲግ በዚህ ይስማማል፦ማቴ ም5ቁ7 ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴርስ ይመልሱታል፦ 1ኛ ከደርግ መንግሥት ጋር በነበረው ግብ ግብ መነሻው ሰሜን ቢሆን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሕዝቦች ደማቸውን አፍስሰው እኩል ከገባን በኁላ የአንድ ብሔር የበላይነት እስካሁን አለ ለምን፦ 2ኛሕገ መንግሥቱ ሲረቀቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደባለቤት ተወያይቶ አላጸደቀውም ችግሩም የተፈጠረው በዚሁ ምክንያት ነው ይላሉ 3ኛ መንግሥት ሕዝቡን ይንቃል አያከብርም ይላሉ፦ 4ኛየኢትዮጵያ ሕዝብና መሬት አንድ ሆኖ ሳለ በብሕር በቁዋንቁዋ በመከፋፈል መከለል ለምን አሰፈለገ፦5ኛየቀበሌ መታወቂያና የመኪና ታርጋ ለምን በብሔር ተደረገ ፦ 6ኛየአሰብ ወደብ የአፋር ሆኖ ሳለ ለምን ተወሰደ ኢትዮጵያስ ያለወደብ ለምን ቀረች 7ኛየኢዮጵያ ሰንደቅ አላማ ወይም ፓዲራ አረንጉዋዴ ብጫ ቀይ ሆኖ ሳለ ብሔር ብሔረሰቦችን ይወክላል ተብሎ የተለጠፈበት ምንድነው፦ 8ኛየምርጫ እድል ለምን አንደ 1997 በፉክክርና በነጻነት አለሆነም 9ኛየሙስና መስፋፋት የፍርድ ቤት ነጻ አለመሆን ችግሩን ሲአባብሰው ምን መፍትሔ ተሰጠው፦10ኛበየቦታው የተሾሙ ባለሥልጣኖች በራሳቸው ተማምነው እንዳይሰሩ ያደረጋቸውና በስብሰባ ብቻ ጊዜ የሚአሳልፍት ለምንድነው፦ 11ኛየሕዝብ መገናኛ ብዙሐን ቴሌብዥንና ረዲዮ ለምን ታፈነ ፦12ኛ በየትምሕርት ቤቱ የግብረገብ ትምሕርት ባለ መኖሩ ወጣቱ ለሱሰኝነት ተዳርጎአል ይላሉ 13ኛወጣቱ አባል
ካልሆናችሁ በሚል ሰበብ ሥራ አጥቶ መንገድ ተዳዳሪና ስደተኛ ሲሆን መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ፦14ኛመንግሥት የንግድ ሥራውስጥ ገብቶ ተቆጣጥሮታል እኛ ምን እንሥራ ይላሉ 15ኛሕጋዊው ነጋዴና ሕገወጡ ነጋዴ ሳይለይ በግምት እዳ ተጥሎብናል ከስረናል ይላሉ፦ 16ኛመንግሥት በሃይማኖት እየገባ የፈለገውን ይሾማል ያልፈለገውን ይሽራል ይላሉ ለምን 17ኛወጣቱና ሕዝቡ ይህ ሁሉ ሲጠራቀምና መሸከም ሲአቅተው ለውጥ እንፈልጋለን ብሎ ሲወጣ ከሕዝቡ የወጡ ሕዝባዊ ሠራዊት ወድሞቻቸውንና እሕቶቻቸውን እየገደሉና እያሰሩ ጥላቻና ብጥብጡ እየባሰ ሲመጣ መንግሥት የሰጠው ምላሽ ምንድነው፠ 18ኛመንግሥት ሕዝብ ነው ተመርጠው የተሾሙ ባለሥልጣኖች ደግሞ አገልጋይዎች ናቸው ይህ በተግባር የሚገለጠው መቼነው። ከዚህ በላይ ከአንድ እስከ አሥራ ስምንት የቀረቡት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄዎች ናቸው አፋጣኝ መፍትሔ ያሰፈልጋቸዋል እንላለን መልካም የፋሲካ በአል ይሁንልን አሜን የቀረኝ ካለ ጨምሩበት አንድ ቀን እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይመለሳል 1ኛየጴጥ መ ም3ቁ16 ይ መ
No comments:
Post a Comment